የኢትዮጵያውያን  ፡ ሀገራዊ  ፡ ሥልጡንሕዝባዊ  ፡ አንድነት  ። Ethiopians' Citizen Democratic Union | Union Citoyenne Démocratique des Éthiopiens የመርበቢያ ፡ አድራሻ ፤ www.slttunhzb.net የእ-ጦማር ፡ አድራሻ ፤ sh1@ttomar.net ገ_ዐዓ_20160101_ዐማርኛ የኢ.ሀ.ሥ.አ. ፡ የ2016 ፡ ዓ.ም. ፡ መልካም ፡ ምኞት ፡ መልእክት ፡ ለኢትዮጵያ ፡ ሕዝብ ፦ « ዅሉም ፡ ኢትዮጵያዊ ፡ በሀገራዊነቱ ፡ ዐምሐራ፡ ነው !  መነሻውም ፡ መድረሻውም ፡ ኢትዮጵያ ፡ ናት ! » _______ ለንደን ፥ መስከረም ፡ 1 ፡ ቀን ፡ 2016 ፡ ዓ.ም. ። የኢትዮጵያ ፡ ሕዝብ ፡ ሆይ ! የዘመናት ፡ ጌታ ፡ እግዚአብሔር ፥ እንኳን ፡ ለ2016 ፡ ዓ.ም. ፡ በደኅና ፡ አደረሰኽ ፡ እያለ ፥ ውጥን ፡ አካልኽ ፥ የኢትዮጵያውያን ፡ ሀገራዊ ፡ ሥልጡንሕዝባዊ ፡ አንድነት ፡ ( ኢ.ሀ.ሥ.አ. ) ፡ ላዲሱ ፡ ዓመት ፡ የድል ፣ የአንድነት ፣ የነጻነት ፡ እና ፡ የሰላም ፡ ምኞቱን ፡ በፍጹም ፡ ትሕትና ፡ ያቀርብልኻል ። የኢትዮጵያ ፡ ሕዝብ ፡ ሆይ ! ከ1966 ፡ ዓ.ም. ፡ አንሥቶ ፡ ላ49 ፡ ዓመታት ፡ የተፈራረቁብኽን ፡ የውንብድና ፡ አገዛዞች ፡ ለሰባት ፡ ሱባኤ ፡ ታግሠኽ ፥ እንሆ ፡ በ50ኛው ፡ ዓመት ፡ ላይ ፥ ቈርጠኽ ፡ በመነሣት ፥ በኢ.ፌ.ዴ.ሪ. ፡ ስም ፡ ጠላት ፡ የተከለብኽን ፡ የ"አፓርትሀይድ" ፡ ሥርዐት ፡ በፋኖ፟ነ፟ት ፡ የዐርበኝነት ፡ ትግል ፡ ለመገ፟ላገል ፡ ተቃርበኻል ። የዐላማኽ ፡ ርቱዕነት ፡ እንሆ ፡ ገና ፡ ከዥምሩ ፡ ታላላቅ ፡ ድሎችን ፡ አቀዳጅቶኽ ፥ መደምደሚያውን ፥ እመናገሻ ፡ ከተማኽ ፡ ዐዲስ ፡ አበባ ፡ በድል ፡ አድራጊነት ፡ ለመግባት ፡ የአርባ ፡ እና ፡ የኀምሳ ፡ ኪሎሜትር ፡ ጕዳይ ፡ ኾኖልኻል ። ጠላት ፡ ግን ፡ መቼም ፡ ቢኾን ፡ አይተኛልኽምና ፥ ትግልኽን ፡ ጠልፎ ፡ ሊከፋፍልኽና ፡ ድልኽን ፡ ሊያመክንብኽ ፡ ዘወትር ፡ እንደሚጠበብ ፡ ታውቀዋለኽ ። ባንድ ፡ የኢትዮጵያ ፡ ሕዝብ ፡ መኻከል ፥ ለይቶ ፥ "የጉራጌ ፡ ሕዝብ" ፣ "የወላይታ ፡ ሕዝብ" ፣ "የሶማሌ ፡ ሕዝብ" ፣ "የትግሬ ፡ ሕዝብ" ፣ "የኦሮሞ ፡ ሕዝብ" ፣ ወዘተርፈ ፡ ... ፥ የሚለው ፡ በምልክዮሽ ፡ / ፡ በ"ኢምፔሪያሊዝም" ፡ ኀይሎች ፡ መመሪያ ፡ መሠረት ፡ በሰፊ፟ው ፡ የሚ፟ነ፟ዛ፟ው ፡ ይህ ፡ አሳ፟ቻ፟ ፡ አባባል ፦ • ባንድ ፡ ዐምሐራነት ፡ ወይም ፡ ቃል ፡ በቃል ፡ በነጻ ፡ ኢትዮጵያዊ ፡ ሕዝብነት ፡ የተዋሐደውን ፡ መላ፟ ፡ የኢትዮጵያ ፡ ሀገራዊ ፡ ሕዝብ ፡ ነጣጥሎ ፡ ትግልኽን ፡ ያዳክምብኻል ፤ • ኢትዮጵያን ፡ የ"ሕዝቦች" ፡ መራኰቻ ፡ አድርጎ ፥ ምልክዮሽ ፡ በ"አደራዳሪነት" ፡ እመኻል ፡ ተሠይሞ ፥ አንዱን ፡ ካንዱ ፡ እያገዳደረ ፡ በማናከስ ፥ ሀገሪቱን ፡ ለፍጹም ፡ ጥፋት ፡ ሊዳርግብኽም ፡ ይሰናዳል ። ለዚህ ፡ አደጋ ፡ መድኀኒቱ ፡ አንድ ፡ ነው፦ ዅሉም ፡ ለኢትዮጵያዊ ፡ ሀገራዊነቱ ፡ ወይም ፡ ባንድ ፡ ቃል ፡ ለዐምሐራነቱ ፡ ይታገል ! ዐምሐራነት ፡ "ዘር" ፡ አይደለም ፤ የመላ፟ው ፡ የኢትዮጵያ ፡ ሕዝብ ፡ የግብር ፡ ስሙ ፣ ሀገራዊ ፡ ማንነቱ ፡ እንጂ ። መላ፟ ፡ ኢትዮጵያ ፡ የእያንዳንዱ ፡ ሀገራዊ ፡ ኢትዮጵያዊ ፡ የኾነችውን ፡ ያኽል ፥ እያንዳንዱ ፡ ሀገራዊ ፡ ኢትዮጵያዊ ፡ ደግሞ ፡ የመላ፟ ፡ ኢትዮጵያ ፡ ነው ። የሀገራዊነት ፡ መብታችን ፡ ሲከበር ፥ ሰብኣዊ ፡ መብታችንም ፣ ማኅበራዊ ፡ ማንነታችንም ፣ ማንኛቸውም ፡ አለኝታዎቻችን ፡ ዅሉ ፡ ዐብረው ፡ ይከበራሉ ፤ እነዚህን ፡ የመሳሰሉ ፡ ጸጋዎች ፡ ዅሉ ፡ የኢትዮጵያ ፡ እና ፡ የሕዝቧ ፡ የአንድነቱ ፡ ጸጋዎች ፡ መኾናቸው ፡ አይዘነጋም ። የኢ.ፌ.ዴ.ሪ.ን ፡ የ"አፓርትሀይድ" ፡ ሥርዐት ፡ ገርስሶ ፡ ለመጣል ፡ እጫፍ ፡ ደርሰኻል ፤ ነጻ ፡ ያወጣኻቸውን ፡ ወረዳዎች ፡ ዅሉ ፡ በመሸጋገሪያ ፡ መንግሥት ፡ የወረዳ ፡ መዋቅርነት ፡ እየደረጀኽ ፥ ሐሳብ ፡ እና ፡ ልብኽን ፣ ዐይን ፡ እና ፡ እግርኽን ፡ ወደ ፡ መና፟ገሻ ፡ ከተማኽ ፡ ዐዲስ ፡ አበባ ፡ አድርገኽ ፥ መላ፟ ፡ ኢትዮጵያን ፡ በፍጥነት ፡ለመቈጣጠር ፡ ታገል ። ለዚህም ፡ አፈጻጸም ፡ ይረዳኽ ፡ ዘንድ ፥ በሚያዝያ ፡ ወር ፡ 2015 ፡ ዓ.ም. ፡ ኢ.ሀ.ሥ.አ. ፡ አስሰናድቶ ፡ ባስተላለፈልኽ፦ " ሥልጡንሕዝባዊ ፡ የመሸጋገሪያ ፡ መንግሥት ፡ ሀገራዊ ፡ ቅያስ ።" በተሠኘው ፡ ሰነድ ፡ የሰፈረው ፡ የመፍትሔ ፡ ሐሳብ ፡ ( www.slttunhzb.net ) ፡ የተሟላ ፡ መመሪያ ፡ ይኾንልኻል ፡ ሲል ፡ አንድነታዊ ፡ ውጥን ፡ አካልኽ ፡ ኢ.ሀ.ሥ.አ. ፡ ዳግመኛ ፡ በትሕትና ፡ ያሳስብኻል ፤ በትግልኽም ፡ ከጐንኽ ፡ አይለ፟ይ፟ም ፨ ትሑት ፡ አገልጋይኽ ፦ ኢ.ሀ.ሥ.አ.