የኢትዮጵያውያን ፡ ሀገራዊ ፡ ሥልጡንሕዝባዊ ፡ አንድነት ። Ethiopians' Citizen Democratic Union | Union Citoyenne Démocratique des Éthiopiens የመርበቢያ ፡ አድራሻ ፤ www.slttunhzb.net የእ-ጦማር ፡ አድራሻ ፤ sh1@ttomar.net ________________________________ የኢ.ሀ.ሥ.አ. ፡ የ2018 ፡ ዓ.ም. ፡ መልካም ፡ ምኞት ፡ መልእክት ፡ ለኢትዮጵያ ፡ ሕዝብ ፦ « ሊነጋ ፡ ሲል ፡ ይጨልማል ! » _______ ለንደን ፥ መስከረም ፡ 2018 ፡ ዓ.ም. ። የኢትዮጵያ ፡ ሕዝብ ፡ ሆይ ! እንኳን ፡ ለ2018 ፡ ዓ.ም. ፡ በደኅና ፡ አደረሰኽ ፡ እያለ ፥ መጪው ፡ ዓመት ፡ የመሥዋዕትኽን ፡ ፍሬ ፡ የምታይበት ፡ ዓመት ፡ እንዲኾንልኽ ፡ ውጥን ፡ አካልኽ ፡ የኢትዮጵያውያን ፡ ሀገራዊ ፡ ሥልጡንሕዝባዊ ፡ አንድነት ፡ ( ኢ.ሀ.ሥ.አ. ) ፡ ከልብ፟ ፡ ይመኛል ። የኢትዮጵያ ፡ ሕዝብ ፡ ሆይ ! ነገር ፡ ዅሉ ፡ እልኩ፟ ፡ ደርሷል ፤ የተፈጥሮ ፡ ሕግ ፡ ነውና ፥ ከልኩም ፡ አያልፍ ። ግፈኞች ፡ እጆቹን ፡ እና ፡ እግሮቹን ፡ በኢትዮጵያ ፡ ምድር ፡ የምታያቸው ፡ ጥንተ ፡ ጠላትኽ ፡ ኢምፔሪያሊዝም ፥ ዛሬ ፥ ተራውን ፥ የፈተና ፡ ዘመንን ፡ ሊቀምስ ፡ ተቃርቦ ፡ ይታየናል ። ከንግዲህ ፡ ዘመኑ ፡ የፈጣን ፡ መሠረታዊ ፡ ለውጥ ፡ ነው ። የመገላገያውን ፡ ምዕራፍ ፡ ጨክኖ ፡ በአንድነት ፡ ታግሎ ፡ ከመሻገር ፡ ሌላ ፡ ማማረጫ ፡ የለምና ፥ የኢ.ፌ.ዴ.ሪ. ፡ የውንብድና ፡ አገዛዝን ፡ በማስወገድ ፥ ሀገራዊ ፡ እግዚእናኽ ፡ ወደሚከበርበት ፡ የመሸጋገሪያ ፡ መንግሥት ፡ ትግልኽን ፡ አጠናክረኽ ፡ ቀጥል ። ኢ.ሀ.ሥ.አ. ፡ ያቀረበልኽ ፦ "ሥልጡንሕዝባዊ ፡ የመሸጋገሪያ ፡ መንግሥት ፡ ሀገራዊ ፡ ቅያስ ።" ( www.slttunhzb.net ) እያደር ፡ የብዙኃኑን ፡ ድጋፍ ፡ እያገኘ ፡ ስለ ፡ ኼደ ፥ በ2018 ፡ ዓ.ም. ፡ የመዠመሪያ ፡ ፍሬዎቹን ፡ ታያለኽ ፡ ሲል ፡ ኢ.ሀ.ሥ.አ. ፡ ሙሉ ፡ እምነቱን ፡ በድጋሚ ፡ ይገልጽልኻል ፨ ትሑት ፡ አገልጋይኽ ፦ ኢ.ሀ.ሥ.አ.