የኢትዮጵያውያን ፡ ሀገራዊ ፡ ሥልጡንሕዝባዊ ፡ አንድነት ። Ethiopians' Citizen Democratic Union | Union Citoyenne Démocratique des Éthiopiens የመርበቢያ ፡ አድራሻ ፤ www.slttunhzb.net የእ-ጦማር ፡ አድራሻ ፤ sh1@ttomar.net ________________________________ ገ_ት-ድበ_20160827_ዐማርኛ የኢ.ሀ.ሥ.አ. ፡ የትንሣኤ ፡ እና ፡ የድል ፡ በዓል ፡ መልካም ፡ ምኞት ፡ መልእክት ፡ ለኢትዮጵያ ፡ ሕዝብ ፦ « የኢትዮጵያዊ ፡ ሀገራዊነት ፡ ትንሣኤ ፡ እና ፡ ድል ፡ በዐምሐራነት ፡ ዳግም ፡ ተበሠረ ! » _______ ለንደን ፥ ሚያዝያ ፡ 27 ፡ ቀን ፡ 2016 ፡ ዓ.ም. ። የኢትዮጵያ ፡ ሕዝብ ፡ ሆይ ! እንኳን ፡ ለጌታችን ፡ ለመድኀኒታችን ፡ ኢየሱስ ፡ ክርስቶስ ፡ የትንሣኤ ፡ በዓል ፡ እና ፡ ለኢትዮጵያ ፡ ሀገራዊ ፡ ድል ፡ በዓል ፡ በሰላም ፡ አደረሰኽ ፡ እያ፟ለ ፥ ሕዝባዊ ፡ አንድነታዊ ፡ ውጥ፟ን ፡ አካልኽ ፥ የኢትዮጵያውያን ፡ ሀገራዊ ፡ ሥልጡንሕዝባዊ ፡ አንድነት ፡ ( ኢ.ሀ.ሥ.አ. ) ፡ መልካም ፡ ምኞቱን ፡ በትሕትና ፡ ያቀርብልኻል ። የትንሣኤ ፡ በዓልንና ፡ የድል ፡ በዓልን ፡ 83ኛ ፡ ዓመት ፡ አንድጋ ፡ በምናከብርበት ፡ ዕለት ፡ በሚያዝያ ፡ 27 ፡ ቀን ፡ 2016 ፡ ዓ.ም. ፥ ሀገራችን ፡ ኢትዮጵያ ፡ እጅግ ፡ አስቸጋሪዎች ፡ ስያሳውያን፣ ጥርየታውያን፣ ማኅበራውያን ፡ እና ፡ ደኅንነታውያን ፡ ችግሮች ፡ ገጥመዋት ፡ ትገኛለች ። የኢትዮጵያ ፡ ሕዝብ ፡ ሆይ ! የእነዚህ ፡ ችግሮች ፡ ዋነኛው ፡ መነሻ ፥ ሀገራዊ ፡ እግዚእናኽን ፡ እስካኹን ፡ ባለማስከበርኽ፣ ሕገ ፡ መንግሥትኽን ፡ ባለመሥራትኽ፣ ሥልጡንሕዝባዊ ፡ መንግሥትኽንም ፡ ባለማቆምኽ ፥ መላ፟ ፡ ሀገርኽ ፡ ለውጭ ፡ ኀይሎች ፡ እሚታዘዙ ፡ የውንብድና ፡ አገዛዞች ፡ ሥር ፡ መውደቋ ፡ መኾኑን ፡ ዐውቀኸዋል ። መፍትሔውን ፡ በመሻት ፥ በኢትዮጵያዊ ፡ ሀገራዊነት ፡ (በዐምሐራነት) ፡ በተደራጁ ፡ የቍርጥ ፡ ቀን ፡ ዠግኖች ፡ ልጆችኽ ፡ ፋኖ፟ዎች ፡ መሥዋዕትነት ፥ ሀገራዊ ፡ እግዚእናኽን ፡ ለማስከበር ፡ በመኻል ፡ ኢትዮጵያ ፡ የትጥቅ ፡ ትግሉን ፡ ባስደናቂ ፡ ውጤት ፡ አጧጡፈኸዋል ፤ መና፟ገሻ ፡ ከተማኽን ፡ ዐዲስ ፡ አበባንም ፡ ለመቈጣጠር ፡ ጥቂት ፡ ቀርቶኻል ። ኾኖም ፥ ትግሉ ፡ መላ፟ ፡ ኢትዮጵያን ፡ እና ፡ መላ፟ውን ፡ የኢትዮጵያ ፡ ነጻ ፡ ሕዝብ ፡ የሚያዳርስ ፡ ትግል ፡ መኾን ፡ ስለሚገ፟ባ፟ው ፥ የፋኖ፟ነ፟ት ፡ ድርጅትኽን ፡ ባ14ቱም ፡ የኢትዮጵያ ፡ ክፍላተ ፡ ሀገር ፡ ውስጥ ፡ በሥልጡንሕዝባዊ ፡ መንገድ ፡ አስፋፍተኽ ፡ ልታጠናክረው ፡ ትችላለኽ ። ለዚህም ፡ ግብ ፥ የፋኖ፟ ፡ ትግልን ፡ በሙሉ ፡ ዐቅምኽ ፡ እንድትደግፈውና ፡ በገፍ ፡ እንድት፟ቀ፟ላቀለው ፡ ኢ.ሀ.ሥ.አ. ፡ የሀገር ፡ ፍቅር ፡ ጥሪውን ፡ በታላቅ ፡ አክብሮት ፡ ያስተላልፍልኻል ። የፋኖ፟ ፡ መሪዎችም ፡ የኢትዮጵያን ፡ ሕዝብ ፡ እግዚእና ፡ በማክበር ፥ የሥልጣን ፡ ውክልናቸውን ፡ ከኢትዮጵያ ፡ ሕዝብ ፡ ለማግኘት ፡ ሙሉ ፡ ፈቃደኝነታቸውን ፡ በገቢር ፡ ሊያሳዩኽ ፡ ይጠ፟በ፟ቅባ፟ቸዋል ፤ ውክልናኽን ፡ ሳያገኙም ፡ በስምኽ ፡ እና ፡ በኢትዮጵያ ፡ ስም ፡ አንዳችም ፡ ስምምነት ፡ ከሦስተኛ ፡ አካል ፡ ጋራ ፡ እንዳይስማሙ ፡ ባክብሮት ፡ እናሳስባለን ። የትግልኽ ፡ ዐላማ ፦ • ሀገራዊ ፡ እግዚእናኽን ፡ ማስከበር ፥ • ዐዲስ ፡ ሕገ ፡ መንግሥትኽን ፡ መሥራት ፥ • ሥልጡንሕዝባዊ ፡ የርትዕ ፡ መንግሥትኽን ፡ መመሥረት ፡ ስለ ፡ ኾነ ፥ ዝርዝር ፡ ክንዋኔያቸው ፡ በደኅና ፡ እና ፡ በተቀላጠፈ ፡ መንገድ ፡ የሚፈጸምበትን ፡ አገባብ ፦ "ሥልጡንሕዝባዊ ፡ የመሸጋገሪያ ፡ መንግሥት ፡ ሀገራዊ ፡ ቅያስ" ( www.slttunhzb.net ) በሚል ፡ ስያሜ ፡ ኢ.ሀ.ሥ.አ. ፡ ቀደም ፡ ሲል ፡ ያቀረበልኽ ፡ ሰነድ ፡ እስካኹን ፡ በከፊል ፡ እንዳገለገለኽ ፡ ዅሉ ፥ ከእንግዲህ ፡ ደግሞ ፡ በሙሉ ፡ እያገለገለኽ ፥ ሀገራችን ፡ ኢትዮጵያን ፡ ባጪር ፡ ጊዜ ፡ ውስጥ ፡ ከጥፋት ፡ እንታደግበታለን ፡ ብሎ ፡ ያምናል ፤ በትግልኽም ፡ ከጐንኽ ፡ አይለ፟ይ፟ም ፨ ትሑት ፡ አገልጋይኽ ፥ ኢ.ሀ.ሥ.አ.