የኢትዮጵያውያን  ፡ ሀገራዊ  ፡ ሥልጡንሕዝባዊ  ፡ አንድነት  ። Ethiopians' Citizen Democratic Union | Union Citoyenne Démocratique des Éthiopiens www.slttunhzb.net sh1@ttomar.net _______ መስከረም ፡ 1 ፡ ቀን ፡ 2014 ፡ ዓ.ም. ። የኢ.ሀ.ሥ.አ. ፡ የ2014 ፡ ዓ.ም. ፡ መልካም ፡ ምኞት ፡ መልእክት ፡ ለኢትዮጵያ ፡ ሕዝብ ፦ የሙት ፡ ይዘት ፡ ትድገት ፥ የለም ፡ በዐዲስ ፡ ዓመት ! _______ ገ_ዐዓ_20140101_ዐማርኛ የኢ.ሀ.ሥ.አ. ፡ የ2014 ፡ ዓ.ም. ፡ መልካም ፡ ምኞት ፡ መልእክት ፡ ለኢትዮጵያ ፡ ሕዝብ ፦ የሙት ፡ ይዘት ፡ ትድገት ፥ የለም ፡ በዐዲስ ፡ ዓመት ! _______ ለንደን፥ መስከረም ፡ 1 ፡ ቀን ፥ 2014 ፡ ዓ.ም.። የኢትዮጵያ ፡ ሕዝብ ፡ ሆይ! ላለፉት ፡ ሠላሳ ፡ ዓመታት ፦ • ላልሠራኸው፡"ሕገ፡መንግሥት" ፣ ለሕገ ፡ ውንብድና ፡ ካልተገዛኽ ፡ እያለ ፡ ሲጨቍንኽ፥ • የኢትዮጵያ ፡ አንድያ ፡ ባለቤትነትኽን ፡ በመካድ ፡ "ሕዝቦች" ፡ እያለ ፡ እየመነዘረኽ ፡ ሀገርኽ ፡ ኢትዮጵያን ፡ ባለቤት ፡ አልባ ፡ ሲያደርግብኽ ፥ • እንደ ፡ እንስሳ ፡ በ"ክልል" ፡ ሲያግድኽ ፥ • ከታሪካውያን ፡ ጠላቶችኽ ፡ ጋራ ፡ ለጥፋትኽ ፡ ሲዶልትብኽና ፡ ባለቤት ፡ አልባ ፡ ሀገርኽን ፡ ሲቈራርስብኽና ፡ ሲያስበዘብዝብኽ ፡ የኖረውን ፡ ከሓዲውንና ፡ ንኅለተኛውን ፡ የኢ.ፌ.ዴ.ሪ. ፡ ይዘት ፥ እንሆ ፥ በአንድነት ፡ ክንድኽ ፡ ዐናቱን ፡ ወያኔ-ሕ.ወ.ሐ.ት.ን ፡ ቀልተኽ ፡ ብታሽቀነጥርበትም ፥ ቅሬታ ፡ አካሉ ፡ "ኢ.ሕ.አ.ዴ.ግ.-ብልጽግና፡ፓርቲ-ሸኔ" ፡ ባፈሰሰለት ፡ የመሰንበቻ ፡ ዐቅም ፡ አንሰራርቶ ፥ አረመኔያዊ ፡ የፈሪ ፡ በትሩን ፡ ዳግም ፡ ሲያሳርፍብኽ ፡ ከርሟል ። አንተም ፡ ልትመክተውና ፡ ፈጽመኽ ፡ ልትደመስሰው ፡ ቈርጠኽ ፡ በመነሣት ፥ የተቀላ፟ ፡ ራሱ ፡ ወደወደቀበት ፡ ወደ ፡ ሰሜን ፡ ኢትዮጵያ ፡ እንሆ ፡ ተመ፟ኻል ። "የዐዞ ፡ ክፋቱ ፥ ፊት ፥ ጥርሱ ፤ ዃላ ፥ ጅራቱ ።" ነውና ፥ ዐዲስ ፡ አበባ ፡ ተቈርጦ ፡ እና ፡ አድብቶ ፡ የቈየ ፡ ቅሬታ ፡ አካሉን ፡ ፈጥነኽ ፡ ካላስወገድከውና ፡ መላ፟ ፡ ሀገርኽ ፡ ኢትዮጵያን ፡ መልሰኽ ፡ እእጅኽ ፡ ካላገባኻት ፡ በቀር ፥ አኹንም ፡ ከዠርባኽ ፡ ተከድተኽ ፡ መሥዋዕትኽ ፡ ዅሉ ፡ አላንዳች ፡ ጥርጥር ፡ ከንቱ ፡ ይኾንብኻል ። ዐዲሱ ፡ ዓመት ፡ 2014 ፡ ዓ.ም. ፥ የፍጹም ፡ ድል ፡ ዓመት ፡ እንዲኾንልኽ ፥ ሕዝባዊ ፡ አንድነታዊ ፡ ውጥን ፡ አካልኽ ፡ የኾነው ፡ የኢትዮጵያውያን ፡ ሀገራዊ ፡ ሥልጡንሕዝባዊ ፡ አንድነት ፡ (ኢ.ሀ.ሥ.አ.) ፡ ከልብ ፡ ይመኝልኻል ። ጥንተ ፡ ጠላትኽን ፡ ፋሺስት ፡ ኢጣልያን ፡ ሚያዝያ ፡ 27 ፡ ቀን ፡ 1933 ፡ ዓ.ም. ፡ በዐርበኞችኽ ፡ ተጋድሎ ፡ ድል ፡ ብታደርጋትም ፥ ፍጹም ፡ ድል ፡ የተገኘው ፡ ግን ፥ ከመንፈቅ ፡ በዃላ ፥ ኅዳር ፡ 18 ፡ ቀን ፡ 1934 ፡ ዓ.ም. ፥ እጥንተ ፡ መዲናኽ ፡ ጐንደር ፡ ላይ ፡ መሽጎ ፡ የነበረው ፡ ቅሬታ ፡ አካሏ ፡ በዐርበኞችኽ ፡ ክንድ ፡ የተደመሰሰ ፡ ዕለት ፡ ነበር ። ዛሬም ፥ በሰማንያኛ ፡ ዓመቱ ፥ ባዲሱ ፡ ዓመት ፡ መባቻ ፥ ፈጽመኽ ፡ በምትተማመንበት ፡ አምላክኽ ፡ በእግዚአብሔር ፡ ኀይል ፡ ጸንተኽና ፥ ሀገራዊ ፡ ሰራዊትኽን ፡ በጠራ፟ ፡ አመራር ፡ እፊትኽ ፡ አስሰልፈኽ ፦ 1) ወያኔ-ሕ.ወ.ሐ.ት.ን ፡ ፈጽመኽ ፡ የምትደመስስበትና ፥ አለቆቹን ፡ ለፍርድ ፡ የምታቀርብበት ፥ 2) የወያኔ-ሕ.ወ.ሐ.ት. ፡ ቅሬታ ፡ አካል ፡ የኾነውን ፡ የኢ.ፌ.ዴ.ሪ. ፡ ቅሬታ ፡ ይዘት ፡ ገርስሰኽ ፡ በመጣል ፥ ከዛሬዋ ፡ መዲናኽ ፡ ዐዲስ ፡ አበባ ፡ ፈጽመኽ ፡ የምታስወግድበት ፥ 3) መላ፟ ፡ ሀገርኽን ፡ ተቈጣጥረኽ ፥ ዳር ፡ ድንበሯን ፡ የምታስከብርበት ፥ 4) በግፍ ፡ የታሰሩ ፡ ልጆችኽን ፡ የምታስፈታበትና ፡ የምትክስበት ፥ 5) ሀገር ፡ ኢትዮጵያን ፡ የከዱና ፡ ያስበዘበዙ ፣ በደም ፡ የታጠቡ ፡ መንደር ፡ ገነኖችንና ፡ ሆድኛ ፡ ዐዳሪዎች ፡ ግብር ፡ ዐበሮቻቸውን ፡ ለፍርድ ፡ የምታቀርብበት ፥ 6) ሀገራዊ ፡ እግዚእናኽን ፡ በማስከበር ፥ ሥልጡንሕዝባዊት ፡ ኢትዮጵያን ፡ ባዲስ ፡ ሕገ ፡ መንግሥት ፡ (ባዲስ ፡ ክዋኔ) ፡ ዳግም ፡ የምትከውንበት ፥ 7) አንድነትን ፣ ነጻነትን ፣ ፍትሕን ፣ ሰላምንና ፡ ልማትን ፡ የምታገኝበት ፡ ዓመት ፡ እንዲኾንልኽ ፡ የኢትዮጵያውያን ፡ ሀገራዊ ፡ ሥልጡንሕዝባዊ ፡ አንድነት ፡ (ኢ.ሀ.ሥ.አ.) ፡ ከልብ ፡ ይመኝልኻል ፤ በምትፈጽመው ፡ ተጋድሎኽም ፡ ዅሉ ፡ ኢ.ሀ.ሥ.አ. ፡ ከጐንኽ ፡ አይለ፟ይ፟ም ፨ ትሑት፡አገልጋይኽ፦ ኢ.ሀ.ሥ.አ.