የኢትዮጵያውያን ፡ ሀገራዊ ፡ ሥልጡንሕዝባዊ ፡ አንድነት ። Ethiopians' Citizen Democratic Union | Union Citoyenne Démocratique des Éthiopiens www.slttunhzb.net sh1@ttomar.net ዜመ_ኢ-1_20120716_ዐማርኛ ዜና ፡ መግለጫ ። የዐድዋ ፡ ዘላለማዊ ፡ ድል ፡ ባተራማሽና ፡ ባጥፊ ፡ ስያስ ፡ አይደብስም ። ለንደን ፥ መጋቢት ፡ 16 ፡ ቀን ፡ 2012 ፡ ዓ.ም. ። በዓለም ፡ ደረጃ ፡ የተስፋፋውን ፡ እጅግ ፡ አደገኛውን ፡ የ"ኮሮኖ ፡ ተላላፊ" ፡ ወረርሽኝ ፡ ለማሸነፍ ፡ የዓለም ፡ መንግሥታትና ፡ አህጉራውያን ፡ ተቋማት ፡ በሞላ፟ቸው ፡ በሚያስደንቅ ፡ መተባበርና ፡ መናበብ ፡ በሚታገሉበት ፡ በዚህ ፡ ሰዓት ፥ በኢትዮጵያ ፡ ላይ ፡ የተንጠለጠለው ፡ የውንብድና ፡ አገዛዝ ፡ የሀገሪቱን ፡ ህልውና ፡ የሚፈታተን ፡ ባዕድ-መራ፟ሽ ፡ ተልእኮውን ፡ መፈጸሙን ፡ ቀጥሏል ። ኢትዮጵያ ፥ ቅኝ ፡ ገዢነትን ፡ ድል ፡ ባደረገችበት ፡ በየካቲት ፡ 23 ፡ ቀን ፡ 1888 ፡ ዓ.ም. ፡ የዐድዋ ፡ ጦርነት ፡ 124ኛ ፡ ዓመት ፡ መታሰቢያ ፡ ሰሞን ፥ በኢ.ፌ.ዴ.ሪ. ፡ ("የኢትዮጵያ ፡ ፌዴራላዊ ፡ ዴሞክራሲያዊ ፡ ሪፓብሊክ" ) ፡ የ"ኢ.ሕ.አ.ዴ.ግ.-ብልጽግና ፡ ፓርቲ" ፡ የውንብድና ፡ ይዘት ፥ በሌለው ፡ ሥልጣንና ፡ የራሱን ፡ "ሕገ ፡ መንግሥት" ፡ (አንቀጽ ፡ 5) ፡ በመጣስ ፥ "በጉባኤ ፡ አጽድቄያቸዋለኹ" ፡ ያላቸውን ፡ ኹለት ፡ አጥፊዎች ፡ የስያስ ፡ ሰነዶች ፡ ይፋ ፡ አውጥቷል ። በዚህ ፡ አደራረጉ ፥ ያፈጣጠሩን ፡ ዐይነት ፣ የተልእኮውን ፡ ምንነትና ፡ የላኪውን ፡ ማንነት ፡ ለዓለሙ ፡ ዅሉ ፡ ፍንትው ፡ አድርጎ ፡ ከሥ፟ቷል ። እንደ ፡ መግቢያ ፡ የቀረበው ፡ የመዠመሪያው ፡ የስያስ ፡ ሰነድ ፥ በትረካው ፡ ፍጹም ፡ ንኅለተኛ ፡ ("ኒኂሊስት" ) ፡ የኾነውን ፡ ያኽል ፥ የኢትዮጵያ ፡ ተማሪዎች ፡ የሀገራቸውን ፡ ታሪክ ፡ በሀገራዊ ፡ ቋንቋቸው ፡ በዐማርኛ ፡ ከመማር ፡ ከልክሎ ፥ በእንግሊዝኛ ፡ እንዲማ፟ሩት ፡ ያስገድዳል ። ኹለተኛውና ፡ ዋነኛው ፡ የስያስ ፡ ሰነድ ፡ ደግሞ ፥ ላንድ ፡ ሺሕ ፡ ዓመታት ፡ በአንድያ ፡ መንግሥታዊ ፡ ልሳንነት ፡ ያገለገለውን ፡ ዐማርኛ ፡ አካቴውን ፡ በማስወገድ ፥ በምትኩ ፡ 5 ፡ ደባ፟ሎች ፡ የሥራ ፡ ቋንቋዎችን ፡ በ"ደባ፟ዩ ፡ መንግሥት" ፡ ደረጃ ፡ በመመደድ ፥ ርስ ፡ በርሳቸው ፡ ተፎካክረውና ፡ ተራኵተው ፡ የሚጣጣሉበትን ፡ ደበኛ ፡ የቋንቋ ፡ ስያስ ፡ አስተዋውቋል ። የኹለቱም ፡ ስያሶች ፡ የጋራ ፡ ግብ ፥ ለዘለቄታው ፡ ዐማርኛ ፡ በኢትዮጵያና ፡ በአፍሪቃ ፡ የሚኖረውን ፡ ቦታ ፡ በመንሣትና ፡ ተስፋውን ፡ በመቅጨት ፥ በምትኩ ፥ እንግሊዝኛን ፡ አንድያው ፡ ያካባቢው ፡ የሥራ ፡ ቋንቋ ፡ ለማድረግና ፡ ኢትዮጵያዊ ፡ ሀገራዊነትን ፡ ለመደምሰስ ፡ ያለበ ፡ የ124 ፡ ዓመት ፡ ደባ ፡ ነው ። ይህ ፡ በ"ኢ.ሕ.አ.ዴ.ግ.-ብልጽግና ፡ ፓርቲ" ፡ የውንብድና ፡ አገዛዝ ፡ መሣሪያነት ፡ የሚፈጸም ፡ ፀረ ፡ ኢትዮጵያ ፣ ፀረ ፡ አፍሪቃ ፡ እና ፡ ፀረ ፡ ሥልጣኔ ፡ የምልክዮሽ ፡ (የ"ኢምፔሪያሊዝም" ) ፡ ኀይሎች ፡ ድርጊት ፥ በኢትዮጵያና ፡ በመላ፟ ፡ አፍሪቃ ፡ ላይ ፡ በተለየ ፡ መመጻደቅና ፡ ተንኰል ፡ የተቃጣ ፡ የጥፋት ፡ ድርጊት ፡ ነው ። መላ፟ ፡ የኢትዮጵያ ፡ ሕዝብ ፡ ባንድነት ፡ በመቃወም ፡ ያስወግደዋል ፡ ሲል ፡ የኢትዮጵያውያን ፡ ሀገራዊ ፡ ሥልጡንሕዝባዊ ፡ አንድነት ፡ (ኢ.ሀ.ሥ.አ.) ፡ ሙሉ ፡ እምነቱን ፡ ይገልጻል ። በዐድዋ ፡ ድል ፡ ነጻ ፡ ለወጣው ፡ ለመላ፟ው ፡ የአፍሪቃ ፡ የብስ ፡ ሕዝብም ፡ የሐራ ፡ ኢትዮጵያ ፡ ታሪክ ፡ የሐራነቱ ፡ ታሪክ ፥ የ"ዐም ፡ ሐራ" ፡ ልሳን ፡ ዐማርኛም ፡ የነጻነቱ ፡ ልሳን ፡ ስለ ፡ ኾኑ ፥ መቼም ፡ ቢኾን ፡ መላ፟ው ፡ የአፍሪቃ ፡ ሕዝብ ፡ ከኢትዮጵያ ፡ ሕዝብ ፡ ጐን ፡ ይቆማል ፡ ሲል ፡ ኢ.ሀ.ሥ.አ. ፡ ያምናል ። 1 ፤ ደባው ። የተባበሩት ፡ ያሜሪካ ፡ ኹነቶች ፡ ("ዩናይትድ ፡ ስቴይትስ ፡ ኦፍ ፡ አሜሪካ" ) ፥ በእግዝእት ፡ ኢትዮጵያ ፡ የውስጥ ፡ ጕዳይ ፡ ጣልቃ ፡ በመግባት ፥ በግንቦት ፡ ወር ፡ 1983 ፡ ዓ.ም. ፥ "ኢ.ሕ.አ.ዴ.ግ.-ብልጽግና ፡ ፓርቲ" ን ፡ በውንብድና ፡ አገዛዝነት ፡ በኢትዮጵያ ፡ የሥልጣን ፡ ሰገነት ፡ ላይ ፡ አላግባብ ፡ ጕብ ፡ እንዲል ፡ አድርገውታል ። የውንብድና ፡ አገዛዙም ፥ ያን ፡ ጊዜ ፡ በተነገረው ፡ ዕገውጡ ፡ መመሪያ ፡ መሠረት ፥ "ዐዲስ ፡ የቋንቋ ፡ ፖሊሲ" ፡ በሚል ፡ ርእስ ፥ የኢትዮጵያ ፡ ሕዝብ ፡ ሳይጠይቅና ፡ ሳይጠ፟የ፟ቅ ፥ ዐማርኛን ፡ ከሀገራዊ ፡ ልሳንነት ፡ አውርዶ ፡ በመንግሥት ፡ የሥራ ፡ ቋንቋነት ፡ መድቦታል ። በዚህም ፡ ድርጊቱ ፥ ላለፉት ፡ 29 ፡ ዓመታት ፡ ዐማርኛን ፡ ተከታትሎ ፡ ከማድከም ፡ ጋራ ፥ ለእንግሊዝኛ ፡ ርምምድ ፡ በሩን ፡ በሰፊው ፡ ከፍቶ ፡ የግብር ፡ ከፋዩን ፡ ሕዝብ ፡ ገንዘብ ፡ ለዚህኛው ፡ ባዕድ ፡ ቋንቋ ፡ መስፋፊያ ፡ ሲያፈሰው ፡ ቈይቷል ። ከ"ጠቅላይ ፡ ሚኒስትሩ" ፡ አንሥቶ ፡ የማወራኛውን ፡ የለፈፋ ፡ ጊዜ ፡ ባብዛኛው ፡ የተቈጣጠሩት ፡ የይዘቱ ፡ ሹመኛዎችም ፥ "እናገለግላቸዋለን" ፡ የሚሏቸውን ፡ ሀገርና ፡ ሕዝብ ፡ በናቀ ፡ ፍጹም ፡ ዕብሪት ፥ በይፋና ፡ በሥራ ፡ ንግግሮቻቸው ፡ ዅሉ ፥ በዐማርኛ ፡ ውስጥ ፡ እንግሊዝኛን ፡ እየቀላቀሉ ፡ የመናገርን ፡ ነውረኛ ፡ ልማድ ፡ እንዲያስፋፉ ፡ ይዘቱ ፡ በግልጽ ፡ ያበራታቸዋል ። ዛሬ ፡ ደግሞ ፥ የዐድዋን ፡ ድል ፡ በዓል ፡ 124ኛ ፡ ዓመት ፡ መታሰቢያ ፡ ለክፉ ፡ ምክንያት ፡ ጠልፎ ፥ የምልክዮሽ ፡ የአእምሮ ፡ ምንደኛዎች ፡ ልንላቸው ፡ በምንገደደው ፡ ጥቂት ፡ ምሁራን ፡ ሲሰናዱ ፡ የቈዩትን ፡ የማተራመሻና ፡ የማጥፊያ ፡ ስያሶች ፡ እንሆ ፡ ይዘቱ ፡ ሊፈጽማቸው ፡ ይፋ ፡ አውጥቷቸዋል ። 2 ፤ የደባው ፡ መነሻና ፡ መድረሻ ። ኢትዮጵያ ፡ በራሷ ፡ ሥልጣኔ ፡ በ"ሥልጡንሕዝብና" ፡ መሠረት ፡ ላይ ፡ የተከወነች ፡ እግዝእት ፡ ሀገር ፡ ናት ። በታሪክ ፡ የተከታተሉ ፡ የምልክዮሽ ፡ ኀይሎች ፡ ዅሉ ፡ ርሷን ፡ ለማንበርከክና ፡ ለመደምሰስ ፡ ቢሞክሩም ፥ የዐድዋ ፡ አንጸባራቂ ፡ ድል ፡ እንዳስታወሰን ፥ በየጊዜው ፡ ድል ፡ እየኾኑ ፡ ተባረዋል ። ዛሬም ፥ የዘመኑ ፡ የምልክዮሽ ፡ ኀይሎች ፥ በኢትዮጵያ ፡ አንጻር ፡ ዐጕል ፡ እልኽ ፡ ውስጥ ፡ ገብተው ፥ ነጻነቷን ፡ ባጐናጸፋት ፡ ሥልጣኔዋ ፡ ላይ ፡ ስለ ፡ ዘመቱ ፥ የሥልጣኔዋ ፡ መስፋፊያ ፡ ጐዳና ፡ የኾነውን ፡ ልሳን ፡ ዐማርኛን ፥ የሥልጣኔዋ ፡ መንኰራኵር ፡ የኾነውን ፡ ኢትዮጵያዊ ፡ ፊደሏንም ፡ ተከታትለው ፡ ያውካሉ ። ዐማርኛ ፡ በኢትዮጵያ ፡ የሀገራዊነት ፡ ልሳን ፡ የኾነው ፡ ከ3000 ፡ ዓመት ፡ በፊት ፡ ነው ፤ ካ11ኛው ፡ ምእትያ ፡ አንሥቶ ፡ ደግሞ ፡ በግእዝ ፡ ምትክ ፡ የኢትዮጵያ ፡ መንግሥታዊ ፡ ልሳን ፡ ኾኗል ። በዚህ ፡ ረዥም ፡ ዘመን ፥ የተደቀኑበትን ፡ መሰናክሎች ፡ ዅሉ ፡ አንድ ፡ ባንድ ፡ እያለፈ ፡ በችሎታ ፡ ዳብሮ ፥ በተፈጥሮ ፡ በተሰጠው ፡ የመርባት ፡ ጸጋው ፡ የሰበቀለው ፡ ዐማርኛ ፥ ይህን ፡ ሀገራዊ ፡ ሟያውን ፡ በላቂያ ፣ በብቃትና ፡ ባስተማማኝነት ፡ እስከ ፡ ዛሬ ፡ ውሏል ፥ ወደ ፡ ፊትም ፡ ይውላል ። እንደዚሁ ፥ በዘመናችን ፥ እንግሊዝኛ ፥ በተመራጭ ፡ አህጉራዊ ፡ ቋንቋነቱ ፥ ለኢትዮጵያ ፡ የውጭ ፡ ግንኝቶች ፡ ኹሉ ፡ ዐያሌ ፡ አገልግሎቶችን ፡ ውሏል ፤ ወደ ፡ ፊትም ፡ ይውላል ። የ"ኢ.ሕ.አ.ዴ.ግ.-ብልጽግና ፡ ፓርቲ" ፡ የውንብድና ፡ አገዛዝ ፥ ከዐማርኛ ፡ ጋራ ፡ ሌሎች ፡ የኢትዮጵያ ፡ የኅብረተሰብ ፡ ቋንቋዎችን ፥ ኦሮምኛን ፣ ትግሪኛን ፣ ሶማልኛን ፣ ዐፈርኛን ፡ (እንደ ፡ አገውኛ ፣ ሲዳምኛ ፣ ጉራግኛ ፣ ወዘተርፈ ፡ ያሉትን ፡ ቋንቋዎች ፡ በመተው) ፡ በ"ደባ፟ዩ ፡ መንግሥት" ፡ የሥራ ፡ ቋንቋነት ፡ ኰልኵሏቸዋል ። ይህን ፡ ሲያደርግ ፥ እነዚህ ፡ የኅብረተሰብ ፡ ቋንቋዎች ፡ የኢትዮጵያ ፡ ሕዝብ ፡ ያንድነቱ ፡ ቋንቋዎችና ፡ ቅርሶች ፡ እንጂ ፥ የከፊል ፡ ሕዝብ ፡ የግል ፡ ንብረቶች ፡ አለመኾናቸውን ፡ ዘንግቶታል ። የኢትዮጵያ ፡ እግዚእ ፡ ሕዝብ ፡ የሀገራውያኑ ፡ አንድነት ፡ ነው ፤ በቋንቋ ፣ በባህል ፡ መበልጸጉም ፡ የቋሚ ፡ ሥርዐቱን ፡ ሥልጡንነትና ፡ ዐቃፊነት ፡ ይመሰክራል ። የኢ.ፌ.ዴ.ሪ. ፡ አሜሪካ-ሠራሽ ፡ የአፓርትሀይድ ፡ "ሕገ ፡ መንግሥት" ፡ በሐሰት ፡ እንደሚለው ፡ የኢትዮጵያ ፡ ሕዝብ ፡ የ"ሕዝቦች" ፡ ጥርቅም ፡ አይደለም ፤ አንድ ፡ ሀገራዊ ፡ ሕዝብ ፡ እንጂ ። ኢትዮጵያ ፡ በርትዕ ፡ ኹነትነት ፡ ከተቋቋመችበት ፡ ከቀዳማዊ ፡ ምኒልክ ፡ ዘመነ ፡ መንግሥት ፡ ዠምሮ ፡ (982-957 ፡ ቅድመ ፡ ልደተ ፡ ክርስቶስ) ፥ የኢትዮጵያ ፡ ሕዝብ ፡ በግብር ፡ ስሙ ፡ "ዐም ፡ ሐራ" ፡ ወይም ፡ "ነጻ ፡ ሕዝብ" ፡ ተብሎ ፡ በአንድነቱ ፡ ይጠ፟ራ፟ል ፤ የሀገራዊነት ፡ ልሳኑም ፡ ዐማርኛ ፡ ነው ። ኢትዮጵያዊ ፡ ሀገራዊነት ፡ ራሱ ፡ ኢትዮጵያ ፡ አንድ ፡ ሀገራዊ ፡ ልሳን ፡ እንዲኖራት ፡ በባሕርዩ ፡ ያስገድዳል ። ዐማርኛም ፡ የኢትዮጵያ ፡ ሕዝብ ፡ በተዋሕዶው ፡ የሠራው ፡ ሀገራዊ ፡ ልሳኑ ፡ በመኾኑ ፥ ሕዝቡ ፡ በፍጹም ፡ አክብሮትና ፡ ፍቅር ፡ ወዶ ፡ ፈቅዶ ፡ ተቀብሎት ፡ ኖሯል ። "ዐማርኛ ፡ ከሀገራዊ ፡ ልሳንነት ፡ ወደመንግሥት ፡ የሥራ ፡ ቋንቋነት ፡ ይውረድልኝ ፤ 84ቱም ፡ የጎሳ/የኅብረተሰብ ፡ ቋንቋዎች ፡ እኩል ፡ የመንግሥት ፡ የሥራ ፡ ቋንቋዎች ፡ ይኹኑልኝ" ፡ የሚል ፡ ጥያቄን ፡ በየትኛውም ፡ ዘመን ፡ ሕዝቡ ፡ ጠይቆ ፡ አያውቅም ። አኹን ፡ በምንገኝበት ፡ ኹኔታ ፥ ጫናው ፡ ከምልክዮሽ ፡ ኀይሎች ፡ የመጣ ፡ የጥቃትና ፡ የጥፋት ፡ ስልት ፡ ነው ፡ ብለን ፡ ልንደመድም ፡ እንገደዳለን ። ከምልክዮሽ ፡ ጋራ ፥ ምናልባት ፡ ለዚህ ፡ ለባዕዳን ፡ ኀይሎች ፡ የጣልቃ ፡ ገብነት ፡ ድርጊት ፡ ምክንያት ፡ ይኾናል ፡ የምንልበት ፡ አንድ ፡ ከግንዛቤ ፡ ማነስ ፡ የመጣ ፡ ስሕተት ፡ አለ ። እኛ ፡ ኢትዮጵያውያን ፥ ኢትዮጵያን ፡ "ሀገር" ፡ ስንል ፥ ከጎሳ ፡ ማንነት ፡ በላይ ፡ የኾነ ፡ የ"ሥልጡንሕዝብና" ፡ ወይም ፡ የኢትዮጵያዊ ፡ ሥልጣኔ ፡ ርትዐት ፡ የሰበሰባቸው ፡ ሀገራውያን ፥ ባንድነታቸው ፡ ከሰፈሩበት ፡ ብሔር ፡ (ምድር) ፡ ጋራ ፡ በመዋሐድ ፥ የፈጠሩትን ፡ ኹነት ፡ ወይም ፡ መንግሥት ፡ ለማለት ፡ ነው ። ለ"ሀገር" ፡ ምዕራባውያን ፡ "City" ፡ የሚሉት ፡ ቃል ፡ በትርጕም ፡ ይቀርበዋል ። ኢትዮጵያ ፥ በውልደት ፡ ወይም ፡ በነገድ ፡ ላይ ፡ የተመሠረተን ፡ ኹነት ፡ (መንግሥት) ፡ ካለፈችው ፡ 3000 ፡ ዘመን ፡ ኾኗታል ። የሀገራዊነትን ፡ መብት ፡ ያከበረች ፡ ኢትዮጵያ ፥ በታሪኳ ፥ ከራሷም ፡ ዐልፋ ፡ በዓለም ፡ ለተጠቁ ፡ ዅሉ ፡ መጠጊያ ፡ ኾናለች ። ባ5ኛው ፡ ምእትያ ፥ በዐፄ ፡ አልአሜዳ ፡ ዘመነ ፡ መንግሥት ፡ (470-478 ፡ ዓ.ም.) ፥ በሮማዊ ፡ ምልክዮሽ ፡ ተጠቅተው ፡ የተሰደዱትን ፡ የተዋሕዶ ፡ ክርስትና ፡ ሐዋርያት ፡ ተስዐቱ ፡ ቅዱሳንን ፡ ከሮማ ፣ ከግብጽና ፡ ከሶርያ ፡ ተቀብላ ፥ ከኢትዮጵያውያን ፡ ተዋሕዶ ፡ ወገኖቻቸው ፡ ጋራ ፡ በነጻነት ፡ እንዲያመልኩ ፡ አድርጋቸዋለች ። ዛሬ ፥ የኢትዮጵያ ፡ ኦርቶዶክስ ፡ ተዋሕዶ ፡ ሃይማኖት ፡ ተከታዮች ፡ 79 ፡ ሚልዮን ፡ ደርሰዋል ። በ7ኛው ፡ ምእትያ ፥ በዐፄ ፡ አድርዓዝ ፡ ዘመነ ፡ መንግሥት ፡ (595-615 ፡ ዓ.ም.) ፥ በመካ፟ ፡ ገዢዎች ፡ የተሳደዱት ፡ የእስልምና ፡ ተከታዮች ፥ ነቢያቸው ፡ ሙሐመ፟ድ ፡ "ወደ ፡ ኢትዮጵያ ፡ ኺዱ ፤ በዚያች ፡ ሀገር ፡ ማንም ፡ አይጨ፟ቈ፟ንም" ፡ ያላቸውን ፡ ሰምተው ፡ ቢሰደዱ ፥ ኢትዮጵያ ፡ ተቀብላና ፡ አስጠግታ ፥ ሃይማኖታቸውን ፡ በሰላምና ፡ በነጻነት ፡ የመከተል ፡ መብታቸውን ፡ አክብራላቸዋለች ። ዛሬ ፥ ካ18 ፡ ሚልዮን ፡ ያላነሱ ፡ ኢትዮጵያውያን ፡ መስልሞች ፡ በኢትዮጵያ ፡ ይገኛሉ ። የሀገራዊነት ፡ ዕስባት ፡ የኢትዮጵያ ፡ ሕዝብን ፡ መንፈስ ፡ ሠርጾታል ፥ ግዛታዊ ፡ ባህሉንም ፡ ተዋሕዶታል ። ለዚህም ፡ ማስረጃ ፥ በቅኝ ፡ ገዢዎች ፡ ተቈርሳ ፡ የነበረችው ፡ ጥንታዊቷ ፡ የኢትዮጵያ ፡ አካል ፡ ባሕር ፡ ምድር ፡ ("ኤርትራ" ) ፥ በሕዝቧ ፡ ውዴታ ፡ መሠረት ፥ በ1945 ፡ ዓ.ም. ፡ በተባበሩት ፡ መንግሥታት ፡ ውሳኔ ፡ ወደ ፡ እናት ፡ ሀገሯ ፡ ኢትዮጵያ ፡ እንድትመለስ ፡ ሲወሰን ፥ ሕዝቡ ፡ ከጠየቀው ፡ ተዋሕዶ ፡ ውጪ ፥ ለኢትዮጵያዊ ፡ አስተሳሰብ ፡ ፍጹም ፡ ባዕድ ፡ በኾነ ፥ በ"ድበ፟ላ" ፡ ("ፌደሬሽን" ) ፡ መልክ ፡ እንድትገናኝ ፡ ቢወስኑባት ፥ ካሥር ፡ ዓመት ፡ በዃላ ፥ በ1955 ፡ ዓ.ም. ፡ በባይቶ ፡ (በሕዝብ ፡ ምክር ፡ ቤት) ፡ መክራ ፡ ዘክራ ፥ በሙሉ ፡ ድምፅ ፡ በመወሰን ፡ ድበ፟ላውን ፡ ገፍታዋለች ። የኢትዮጵያ ፡ የሕዝብ ፡ ምክር ፡ ቤትም ፡ ውሳኔዋን ፡ በማጽደቅ ፥ በዚያው ፡ ዓመት ፡ 14ኛዋ ፡ የኢትዮጵያ ፡ ጠቅላይ ፡ ግዛት ፡ (ክፍለ ፡ ሀገር) ፡ ኾና ፡ በዐዋጅ ፡ ተመልሳ ፡ ተዋሕዳለች ። ኢትዮጵያውያን ፥ ሕዝብና፟ቸውን ፡ በሀገራዊነት ፡ አገባብ ፡ እንጂ ፥ የኢ.ፌ.ዴ.ሪ. ፡ "ባዕድ-ሠራሽ ፡ የአፓርትሀይድ ፡ ሕገ ፡ መንግሥት" ፡ እንደደነገገው ፥ በውልደቶች ፡ ክፍለት ፡ መልክ ፡ አያዩትም ። ነገር ፡ ግን ፥ ዛሬም ፡ በዚሁ ፡ በውልደት ፡ ላይ ፡ በተመሠረተ ፡ ኹነት ፡ (መንግሥት) ፡ ደረጃ ፡ ለሚገኙ ፡ የውጭ ፡ መንግሥታት ፥ ይህ ፡ ኢትዮጵያ ፡ ጥንት ፡ ያለፈችው ፡ ደረጃ ፡ የላቀ ፡ ደረጃ ፡ ስለሚመስላቸው ፥ ኢትዮጵያም ፡ የዃልዮሽ ፡ "በውልደት ፡ ክፍለት ፡ ተከፋፍላ ፥ ዳግመኛ ፡ በደባ፟ይ ፡ (በ"ፌደራል") ፡ መንግሥትነት ፡ አለዚያም ፡ በተዳባይ ፡ (በ"ኮንፌደራል") ፡ መንግሥትነት ፡ እንዳዲስ ፡ ትዋቀር" ፡ ብለው ፡ በማያገባቸው ፡ ገብተው ፡ ፈቃዳቸውን ፡ በሀገሪቱ ፡ ላይ ፡ በጕልበት ፡ ሊያጸኑባት ፡ ይሞክራሉ ። ከ3000 ፡ ዘመን ፡ በዃላ ፡ በውልደቶች ፡ ድበ፟ላ ፡ ወይም ፡ ተዳብሎ ፡ ("ኮንፌደሬሽን" ) ፡ ኢትዮጵያን ፡ ለማዋቀር ፡ መሞከር ፥ ባንዲት ፡ እግዝእት ፡ ሀገር ፡ የውስጥ ፡ ጕዳይ ፡ ጣልቃ ፡ መግባት ፡ የኾነውን ፡ ያኽል ፥ ፍጹም ፡ አዘብጣጭና ፡ ውድቅ ፡ አደራረግም ፡ ነው ፤ የኢትዮጵያ ፡ ሕዝብ ፡ እስካኹን ፡ አንዳልተቀበለው ፡ ዅሉ ፥ ወደ ፡ ፊትም ፡ ያስወግደዋል ። ለ"ፕሮፐጋንዳ" ፡ ዐላማ ፡ በሰፊው ፡ የሚነ፟ዙ፟ትን ፡ አኃዞች ፡ ወደ ፡ ጐን ፡ ትተን ፥ በኢትዮጵያ ፡ ስለቋንቋ ፡ ተናጋሪዎች ፡ አኃዞች ፡ እውኑን ፡ ስንመለከት ፥ ኹኔታው ፡ እንደሚከተለው ፡ ነው፦ •ዐማርኛ ፡ የ110 ፡ ሚልዮን ፡ ኢትዮጵያውያን ፡ ሀገራዊ ፡ ልሳን ፡ እንደ ፡ መኾኑ ፡ መጠን ፥ በመላ፟ ፡ ሀገሪቱ ፡ ይነገራል ፤ የሀገሪቱ ፡ ትምህርት ፡ ቤቶች ፡ ተማሪዎችም ፡ ይማሩታል ። •ከዐማርኛ ፡ ጋራ ፥ ‣ኦሮምኛ ፡ ተናጋሪ ፥ 15% ፡ (15.4% ፡ የኬንያን ፡ ተናጋሪዎች ፡ ጨምሮ) ፤ ‣ትግሪኛ ፡ ተናጋሪ ፥ 8% ፡ (ባሕር ፡ ምድርን ፡ ጨምሮ) ፤ ‣ሶማልኛ ፡ ተናጋሪ ፥ 5% ፡ (17% ፡ የሶማልያን ፣ የኬንያንና ፡ የጂቡቲን ፡ ተናጋሪዎች ፡ ጨምሮ) ፤ ‣ዐፈርኛ ፡ ተናጋሪ ፥ 1.7% ፡ (2% ፡ የጂቡቲን ፡ ተናጋሪዎች ፡ ጨምሮ) ። እነዚህን ፡ አራት ፡ የኅብረተሰብ ፡ ቋንቋዎች ፡ ከዐማርኛ ፡ ጋራ ፡ "ዐምስቱ ፡ የደባ፟ዩ ፡ መንግሥት ፡ የሥራ ፡ ቋንቋዎች ፡ ይኹኑ" ፡ ብሎ ፡ "ውሳኔ" ን ፡ ማሳለፍ ፡ ራሱ ፥ የይዘቱ ፡ "ሕገ ፡ መንግሥት" ፡ ባ5ኛ ፡ አንቀጹ፦"ዐማርኛ ፡ የደባ፟ዩ ፡ መንግሥት ፡ የሥራ ፡ ቋንቋ ፡ ይኾናል" ፡ ሲል ፡ ያጸናውን ፡ መጣስ ፡ ነው ። ከዚህም ፡ የባሰ ፥ ዐማርኛ ፡ የሀገራዊነት ፡ ልሳን ፡ በኾነበት ፡ ሀገር ፥ ይህን ፡ የመሰለው ፡ "ውሳኔ" ፥ የሀገሪቱን ፡ አስተዳደር ፡ ለማወክ ፥ እድገቷን ፡ ለማሰናከል ፥ ሀገሪቱን ፡ ከፋፍሎ ፥ በምትኳ ፡ ለዘለቄታው ፡ የተዳብሎ ፡ ሥርዐትን ፡ በአፍሪቃ ፡ ቀንድ ፡ ለማዋቀር ፥ ብሎም ፡ እንግሊዝኛን ፡ ያካባቢው ፡ አንድያ ፡ የሥራ ፡ ቋንቋ ፡ ለማድረግ ፥ "በከፋፍለኽ ፡ ግዛ" ፡ ስልትም ፡ የምልክዮሽ ፡ ኀይልን ፡ ባካባቢው ፡ ላይ ፡ ለማንፈራጠጥ ፤ ወይም ፡ ባንድ ፡ ቃል ፥ ሀገርን ፡ ለባዕድ ፡ አሳልፎ ፡ ለመስጠት ፡ ካልኾነ ፡ በቀር ፥ ስያሳዊም ፡ ኾነ ፡ ጥርየታዊ ፡ አንዳች ፡ ጥቅም ፡ አይገኝበትም ። 3 ፤ ተቃውሞና ፡ ትግል ። የ"ኢ.ሕ.አ.ዴ.ግ.-ብልጽግና ፡ ፓርቲ" ፡ የውንብድና ፡ አገዛዝ ፥ የሥልጣን ፡ ተገቢነት ፡ የለውምና ፥ በኢትዮጵያ ፡ ዘላቂ ፡ ጥቅም ፡ ላይ ፡ የሚወስነው ፡ አጥፊ ፡ ውሳኔ ፡ ዅሉ ፡ በመሠረቱ ፡ ውድቅና ፡ ፉርሽ ፡ ነው ። ኾኖም ፥ እስካኹን ፡ እንደታየው ፡ ዅሉ ፥ ይዘቱ ፡ እነዚህንም ፡ የጥፋት ፡ ውሳኔዎቹ ፡ በማናለብኝነት ፡ በገቢር ፡ የሚፈጽማቸው ፡ ከኾነ ፥ የኢ.ፌ.ዴ.ሪ. ፡ ይዘት ፡ ሲወገ፟ድ ፥ ኀላፊዎቹና ፡ ተባባሪዎቻቸው ፡ በሕግ ፡ ፊት ፡ እንደሚጠ፟የ፟ቁ ፡ መታወቅ ፡ አለ፟በ፟ት ። ዘመኑ ፡ በመላ፟ ፡ ዓለም ፡ ዅሉን ፡ ዐይነት ፡ አደጋ ፡ ያዘበዘበበት ፡ አሥጊ ፡ ዘመን ፡ ኾኗል ። ከ"ዘር ፡ ማጽዳት" ፡ ዘመቻ ፡ እስከለየለት ፡ የሥልጣን ፡ ጦርነት ፡ አደጋ ፥ ከድኽነት ፡ እስከ ፡ ረኃብ ፥ ከሙስና፟ ፡ እስከሰብኣዊ ፡ መብት ፡ ጥሰት ፥ ከሕገ ፡ ወጥ ፡ የሰዎች ፡ ዝውውር ፡ እስከ"ሕዳሴ ፡ ግድብ" ፡ ውዝግብ ፥ ካንበጣ ፡ መንጋ ፡ ወረራ ፡ እስከ"ኮሮና ፡ ተላላፊ" ፡ ወረርሺኝ ፥ ኢትዮጵያን ፡ የገጠሟት ፡ አደጋዎች ፡ ብርቱዎች ፡ ናቸው ፤ የቀረውም ፡ ዓለም ፡ ተዘርዝረው ፡ በማያበቁ ፡ አደጋዎች ፡ ተጠምዷል ። ኀላፊነት ፡ የሚሰ፟ማ፟ው ፡ ወገን ፡ ዅሉ ፡ ለማንኛውም ፡ ችግር ፡ በቅድሚያ ፡ ሰላማዊ ፡ መፍትሔን ፡ በገቢር ፡ መሻትና ፡ ሥርዐትን ፡ ማክበር ፡ ይጠበቅበታል ። ሀገር ፡ ላይ ፡ ያንዣበቡት ፡ እነዚህ ፡ ችግሮች ፡ ዅሉ ፡ በሙሉ ፡ ክሂሎትና ፡ በተገቢ ፡ ሥልጣን ፡ ብቻ ፡ የሚ፟ፈ፟ቱ ፡ ስለ ፡ ኾነ ፥ የ"ኢ.ሕ.አ.ዴ.ግ.-ብልጽግና ፡ ፓርቲ" ፡ የውንብድና ፡ አገዛዝ ፥ ይህኑ ፡ እንዲገነዘብና ፥ ከባዕድ ፡ ኀይል ፡ መሣሪያነቱ ፡ ተላቆ፟ ፥ አላግባብ ፡ ከወጣበት ፡ የሥልጣን ፡ ሰገነት ፡ በሰላም ፡ በመውረድ ፥ ቦታውን ፡ በሥልጡንሕዝባዊ ፡ መንገድ ፡ ለሚ፟ሠ፟የ፟ም ፡ የመሸጋገሪያ ፡ መንግሥት ፡ ለማስረከብ ፡ እንዲዘጋጅ ፡ ኢ.ሀ.ሥ.አ. ፡ ዳግመኛ ፡ ያሳስበዋል ። የማንዘነጋው ፡ አንድ ፡ መሠረታዊ ፡ እውነት ፡ አለ ። አንድ ፡ የተደራጀ ፡ አካል ፡ መንግሥታዊ ፡ ኀይልን ፡ በእጀ ፡ መናኛ ፡ ሲይዝ ፥ የሥልጣን ፡ ተገቢነት ፡ የለውምና ፥ እሥልጣኑ ፡ ሰገነት ፡ ላይ ፡ ለመቈየት ፡ ሲል ፡ ብቻ ፥ ለውጭ ፡ ኀይሎች ፡ ታዛዥና ፡ መሣሪያ ፡ ሊኾን ፡ ስኡንነቱ ፡ ራሱ ፡ ያሰላዋል ፥ ያስገድደዋልም ። የዛሬ ፡ 124 ፡ ዓመት ፡ ኢትዮጵያ ፡ የዐድዋን ፡ ድል ፡ ተቀዳጅታ ፡ እግዚእናዋንና ፡ ነጻነቷን ፡ ያስከበረችው ፥ ተፈላጊውን ፡ የሥልጣን ፡ ተገቢነት ፡ ለ3000 ፡ ዓመት ፡ ባረጋገጠችበት ፡ ግዛታዊ ፡ ሥርዐቷ ፡ ተገቢ ፡ ሥልጣንን ፡ በተሠየሙ ፡ ንጉሠ ፡ ነገሥት ፡ ዳግማዊ ፡ ምኒልክ ፡ ብቁ ፡ መሪነት ፡ ነበር ። የጥንቱንም ፡ የዘመኑንም ፡ የኢትዮጵያ ፡ ታሪክ ፡ መለስ ፡ ብለን ፡ ስንመረምር ፥ አብዛኛውን ፡ ጊዜ ፡ ሀገሪቱ ፡ ለሽንፈት ፡ የተዳረገችው ፡ በውንብድና ፡ አገዛዝ ፡ ሥር ፡ በወደቀችበት ፡ የድክመት ፡ ዘመን ፡ እንደነበር ፡ እንገነዘባለን ። ዛሬም ፡ የኢትዮጵያ ፡ ሕዝብ ፡ እግዚእናውን ፡ ፈጥኖ ፡ በማስከበር ፥ ባዲስ ፡ ሕገ ፡ መንግሥት ፡ ወይም ፡ ክዋኔ ፡ ሥልጡንሕዝባዊ ፡ የርትዕ ፡ ኹነቱን ፡ ካላቆመና ፡ ገዢዎቹን ፡ በሥልጡንሕዝባዊ ፡ ሥርዐት ፡ ካልሠየመ ፡ በቀር ፥ አኹን ፡ ጫፍ ፡ ጫፉን ፡ የምናየው ፡ የምልክዮሽ ፡ ደባ ፡ በማንኛውም ፡ ሰዓት ፥ በተለይ ፡ ደግሞ ፡ ድንገት ፡ በሚፈጸም ፡ የክዳት ፡ አደራረግ ፥ ሀገርን ፡ ወደ ፡ ማፈራረስ ፡ እንደሚሸጋገር ፡ አያጠራጥርም ። የኢትዮጵያ ፡ ሕዝብ ፡ የተደቀነበትን ፡ ጊድር ፡ ለመቋቋም ፥ ሕዝባዊ ፡ አንድነታዊ ፡ አካሉ ፡ ለኾነው ፡ ኢ.ሀ.ሥ.አ. ፡ በሠሪ ፡ አባልነቱ ፡ በፍጥነትና ፡ ባገር ፡ ፍቅር ፡ በማበር ፥ ተደራጅቶ ፡ ይነ፟ሣ፟ል፨ የጊዜያዊ ፡ ፈጻሚ ፡ ምክር ፡ ጽሕፈት ፡ ቤት ፥ ኢ.ሀ.ሥ.አ. ። _______  የኢትዮጵያውያን ፡ ሀገራዊ ፡ ሥልጡንሕዝባዊ ፡ አንድነት ። ETHIOPIANS' CITIZEN DEMOCRATIC UNION www.slttunhzb.net sh1@ttomar.net ዜመ_ኢ-1_20120716_እንግሊዝኛ PRESS RELEASE (English translation of the Amharic original) The eternal victory of Adwa will not be eclipsed by disruptive and destructive policies. London, 25th March 2020. While governments and international institutions around the World, acting with remarkable solidarity and coordination, are trying to tackle the terribly threatening "corona virus" pandemic, the dictatorial régime that is clinging to power in Ethiopia is busy taking a step further its foreign assigned mission to the detriment of the very existence of the country. The F.D.R.E. ("Federal Democratic Republic of Ethiopia" ) régime's illegitimate "E.P.R.D.F.-Prosperity Party" led government, has made public two notoriously pernicious policy documents it claims to have adopted in cabinet, without the necessary authority to do so, and in violation of its own "Constitution" (article 5). The announcement coincides with the commemorations of the 124th anniversary of the 2nd of March 1896 Ethiopian victory over colonialism at the battle of Adwa. In so doing, the régime has clearly exposed to the whole world its true nature, the character of its mission, and the identity of its sponsors. The first policy document presented as an appetiser, distinctly nihilistic in its narration, is one which intends to force Ethiopian students to learn the history of their country in the English language instead of the official language of Ethiopia, Amharic. The second policy document, the main course, intends to altogether remove Amharic from the position of unique official language of Ethiopia it held over the past ten centuries, and to level five working languages for the "federal government", thereby condemning these to rival against each other and in the end fail together. The 124 years old common objectives of these two policies are to weaken the overall position and future role of Amharic in Ethiopia and Africa, then to impose English as the unique working language of the region, and ultimately to do away with Ethiopian citizenship. These actions, implemented with particular sophistry and malice by the illegitimate "E.P.R.D.F.-Prosperity Party" led government serving as instrument, are anti-Ethiopia, anti-Africa and anti-civilisation destructive actions carried out on behalf of imperialist forces, to undermine Ethiopia and the whole of Africa. The Ethiopians' Citizen Democratic Union (E.C.D.U.) strongly believes that the Ethiopian people will oppose them in unison and nullify them. The E.C.D.U. also believes that, the people of the African continent will always stand by the side of the Ethiopian people, knowing that the African people consider the history of independent Ethiopia as the history of their independence, and the "language of the free people" Amharic as the language of their freedom. 1: The machination. The illegitimate "E.P.R.D.F.-Prosperity Party" led government, was put in place, back in May 1991, following the interference of the United States government in the internal affairs of sovereign Ethiopia. Without having the expressed wish or consent of the Ethiopian people, and simply following the unlawful directives it was then dictated, the régime implemented its "new language policy" which consisted in downgrading the Amharic language from the position of "official language" to that of "working language of government". In so doing, it has over the past 29 years systematically undermined the Amharic language, while holding the door wide open for the English language and spending taxpayers' money for the promotion of this foreign language. The régime is further openly encouraging all its apparatchiks, starting from the "prime minister", to use their control over media broadcasting time for the popularization of the reprobate habit of mixing English in their official Amharic pronouncements, in full contempt for the country and the people they claim to serve. Of all occasions, the régime has now chosen the celebrations of the 124th anniversary of the Victory of Adwa to make public these disruptive and destructive policies that had been in the making by those few intellectuals we are now forced to call intellectual mercenaries of imperialism. 2: Cause and finality of the machination. Ethiopia is a millennia old sovereign country, established on the foundations of her own civilisation, "ሥልጡንሕዝብና". Forces of imperialism that have appeared and gone in history, have all attempted to subjugate and annihilate her; but as the resounding victory of Adwa reminded us, they were each time defeated and repelled. Likewise, today's imperialist forces have entered into an inauspicious obstinacy to overcome her civilisation, by systematically disrupting the highway of her civilisation: Amharic, and the vehicle of her civilisation: the Ethiopic writing system. Amharic has been the language of citizenship in Ethiopia for the past three millennia, and, replacing the G'z language, it has been the language of government since the 11th century A.D. Over this long period, Amharic, a language naturally endowed with powerful generative attributes, has developed into a versatile and sophisticated language by overcoming one by one all the obstacles it encountered to eminently, satisfactorily and reliably serve the country; and it will continue to do so in future. Similarly, the English language, as an international language of choice, has played a tremendous role in Ethiopia's external relations, and will continue to do so in future. The illegitimate "E.P.R.D.F.-Prosperity Party" led government has chosen to put on par with Amharic other Ethiopian communal languages, namely Oromgna, Tgrigna, Somalgna and Afergna, as the working languages of the "Federal Government" (forsaking such other languages as Agewgna, Sidamgna, Gurag-gna, etc.). In so doing, the régime appears to ignore that these communal languages are not the private property of sections of the population, but rather belong to the unity of the Ethiopian people. The sovereign people of Ethiopia are the unity of Ethiopian citizens; their blessedness with diverse languages and traditions attest of the civil and tolerant nature of their pre-existent political system. Contrary to what the US-made Apartheid "Constitution" falsely proclaims, the Ethiopian people are not a hodgepodge of peoples, but a citizenry. Ever since Ethiopia was reconstituted as a State of Right during the reign of Emperor Mnilk Ist (974-949 B.C.), the Ethiopian people have been known in their unity by their constitutive name "Amhara" or "Free People"; and their language of citizenship has always been Amharic. Ethiopian citizenship, by its very nature, requires that Ethiopia has a single language of citizenship. Since Amharic is the language that the Ethiopian citizenry have crafted by their union, it has always earned their unanimous respect, love and acceptance. There is no time in history where the Ethiopian people have requested that "the Amharic language be downgraded from the position of official language to that of working language of government", nor have they ever requested that "all communal languages, all 84 of them, be the working language of government". We are forced to deduce, under present circumstances, that the pressure comes from the forces of imperialism whose tactical goals are disruption and destruction. Together with imperialism, there is probably also, a degree of lack of awareness on the part of the foreign forces involved, explaining their unlawful actions. What Ethiopians call "ሀገር" when speaking of Ethiopia, beyond and above ethnic identity, is in fact the State of Right that the people, having rallied round the ideals of their civilisation of Right "ሥልጡንሕዝብና", have established through their union with the territory they inhabited. The term that most closely translates "ሀገር" is the Western term of "City". Ethiopia has gone past the State based on ethnicity some 3000 years ago. Respectful of citizen rights, Ethiopia has always been in her history a safe haven for victims of persecution, beyond her own people. In the 5th century A.D., during the reign of Emperor Elaméda (478-486 A.D.), she gave refuge to nine saints of the Orthodox Tewahdo Church who fled from the persecution of Roman imperialism in Rome, Egypt and Syria, and allowed them to practice freely their faith with their co-religionists in Ethiopia. Today the Ethiopian Orthodox Tewahdo Church has some 79 million followers in Ethiopia. In the 7th century A.D., during the reign of Emperor Adrʼaz (602-623 A.D.) the followers of Islam fled to Ethiopia, when the rulers of Mecca persecuted them. They chose Ethiopia because their Prophet Muhammed had told them it was the land where no one is persecuted. Today some 18 million Muslims freely practice their faith in Ethiopia. The concept of citizenship is ingrained in the spirit of the Ethiopian people and fused with their political culture. A recent proof of that is the manner in which the province of Bahr Mdr (Eritrea) which was separated from her motherland Ethiopia by colonialism, was finally reunited with Ethiopia. In 1952, Bahr Mdr was joined to Ethiopia when the United Nations adopted their resolution, based on the wishes of the majority of the inhabitants of the territory. However, contrary to the pure and simple reunification that the population of the territory had requested, the United Nations decided instead to opt for a federal arrangement, which was anathema to the Ethiopian spirit. Ten years later, in 1962, the "Bayto" or parliament of Bahr Mdr unanimously passed a resolution rejecting the federation in favour of unification with Ethiopia. Bahr Mdr became the 14th province of Ethiopia with the ratification and enactment of that decision by the Ethiopian parliament in that same year. Ethiopians perceive the Ethiopian people in terms of citizenship, and not in terms of a partition of different ethnicities, as the F.D.R.E. régime's "foreign inspired apartheid constitution" wrongly stipulates. Some of those foreign countries that are until today established on the principles of Nation-State and therefore consider themselves to be at the forefront of "State evolution", have taken the further out of place and unlawful steps of forcefully imposing the retrograde partitioning of Ethiopia along ethnic lines before it is reconstituted anew into a federal or a confederal entity. These retrograde acts, as much as they are an interference in the internal affairs of a sovereign country, they are null and void; as such, the Ethiopian people have not accepted them, and will invalidate them in the end. Leaving out the statistics that are widely disseminated for propaganda purposes, the language speakers' statistics of Ethiopia, as they are observable on the ground, are as follows: •Amharic is the language of citizenship of a country of 110 million people, it is spoken in the whole country, and is taught in each and every school in the land; •With Amharic: ‣Oromgna speakers, 15% (15.4%, including speakers in Kenya); ‣Tgrigna speakers, 8% (including Bahr Mdr); ‣Somalgna speakers, 5% (17%, including speakers in Somalia, Kenya and Djibouti); ‣Afergna speakers, 1.7% (2%, including speakers in Djibouti); To try to impose by "decree" these four communal languages together with Amharic as the "five working languages of the federal government", is to violate the régime's own "Constitution" which proclaims that: "Amharic shall be the working language of the Federal Government." But, more importantly, in a country where Amharic has always been the language of citizenship, this "decree" has no political or economic justification, other than the wicked design of hampering the administration of the country, of thwarting its growth, of partitioning the country to set up in its place a confederal system in the Horn of Africa and eventually of imposing English as the only working language of government, to ultimately establish, with the divide and rule tactics, a stronghold for imperialism in the region; in short: to hand over the country to foreign powers. 3: Opposition and struggle. All decisions by the illegitimate "E.P.R.D.F.-Prosperity Party" led government that are detrimental to the permanent interests of Ethiopia are, a priori, null and void. Nevertheless, if the régime persists in implementing its latest destructive decisions without any concern for legality, as we have witnessed so far, then it is clear that, upon its removal, its officials and collaborators will be held liable before the law. Everywhere in the world, we are living in times of impending disaster. From "ethnic cleansing" to the possibility of an all-out civil war, from poverty to famine, from corruption to human rights abuse, from illegal human trafficking to the "Renaissance dam" dispute, from the locust plague to the "corona virus" pandemic, the dangers Ethiopia is facing are grave; the rest of the world too is beset by an endless list of impending perils. In these circumstances, we should expect from all responsible sides that they prioritise peaceful solutions to all issues, as well as respect legality. The dangers that are looming over our country can only be addressed with the full potential of the country harnessed by a legitimate authority. That is why the E.C.D.U. once again launches an appeal to the illegitimate "E.P.R.D.F.-Prosperity Party" led government, to recognise these facts, and cease from serving as an instrument to foreign powers by stepping down from the positions of power and give way for a democratically elected transitional government. We should not forget one essential truth however: any organised body that usurps the instruments of State power is inclined and forced to submit to foreign powers and serve their interests for the sake of staying in power, as its lack of legitimate authority makes it fundamentally weak. Ethiopia was able to reassert her sovereignty and safeguard her liberty with the victory of Adwa, 124 years ago, thanks to the capable leadership of Emperor Mnilk II, who was the legitimate head of the Ethiopian political system which has the merit of upholding, over the past 3000 years, the indispensable principle of legitimacy of authority. When we examine the ancient and contemporary history of Ethiopia, we find that the occasions where the country experienced defeat at the hands of external forces coincided mostly with periods of weakness where usurpers were at the helm. Today, unless the Ethiopian people rapidly reassert their sovereignty, re-establish their democratic State of Right on the basis of a new Constitution, and democratically elect their government, then the machinations of imperialism, of which we only see the tip, will undoubtedly and in a sudden and deceitful turn, escalate into an attempt on the very existence of the country. The Ethiopian people will rise up to the challenge in an organised manner by quickly reinforcing, through their active and patriotic engagement, the embodiment of their popular unity, the E.C.D.U.. Secretariat of the Provisional Executive Council, E.C.D.U. _______ የኢትዮጵያውያን ፡ ሀገራዊ ፡ ሥልጡንሕዝባዊ ፡ አንድነት ። UNION CITOYENNE DÉMOCRATIQUE DES ÉTHIOPIENS www.slttunhzb.net sh1@ttomar.net ዜመ_ኢ-1_20120716_ፈረንሳይኛ COMMUNIQUÉ DE PRESSE (traduction française de l'original en amharique) L'éternelle victoire d'Adwa ne sera pas éclipsée par des politiques disruptives et destructives. Londres, le 25 mars 2020. Alors que les gouvernements et les institutions internationales, agissant à l'échelle mondiale avec une remarquable solidarité et concertation, s'acharnent à faire face à la pandémie du "corona virus" si menaçante, le régime dictatorial qui s'accroche toujours au pouvoir en Éthiopie, est, lui, occupé à mener plus loin la mission qui lui a été assignée de l'extérieur, au détriment de l'existence même du pays. Le gouvernement "E.P.R.D.F.-Parti de la Prospérité" illégitime du régime R.F.D.E. (République Fédérale Démocratique d'Éthiopie) a rendu publics deux documents politiques particulièrement pernicieux qu'il dit avoir adoptés en conseil des ministres, sans qu'il ait une quelconque autorité, et en violation de sa propre "Constitution" (article 5). Cette annonce coïncide avec les célébrations du 124ème anniversaire de la victoire éthiopienne sur le colonialisme, durant la bataille d'Adwa, le 2 mars 1896. Ce faisant, le régime a clairement exposé au monde entier sa vraie nature, le caractère de sa mission, ainsi que l'identité de ses commanditaires. Le premier document politique présenté en entrée, clairement nihiliste dans sa narration, a l'intention de forcer les étudiants éthiopiens à apprendre l'histoire de leur pays dans la langue anglaise, à la place de la langue officielle de l'Éthiopie, l'amharique. Le second document politique, véritable plat de résistance, se targue de détrôner l'amharique de la position d'unique langue officielle de l'Éthiopie qu'elle occupe depuis dix siècles, et de niveler cinq langues de travail au niveau du "gouvernement fédéral", lesquelles seront condamnées à se rivaliser entre elles, pour finir ensemble en échec. Les objectifs communs à ces deux politiques, vieux de 124 ans, sont l'affaiblissement de la position et du rôle avenir de l'amharique en Éthiopie et en Afrique, puis l'imposition de l'Anglais comme unique langue de travail de la région, et enfin la suppression même de la citoyenneté éthiopienne. Ces actions, exécutées par un gouvernement "E.P.R.D.F.-Parti de la Prospérité" illégitime, pour le compte des forces impérialistes, avec un sophisme et une malice particuliers, sont anti-éthiopiennes, anti-africaines et anti-civilisation, visant à contrecarrer l'Éthiopie et l'ensemble de l'Afrique. L'Union Citoyenne Démocratique des Éthiopiens (U.C.D.E.) croit fermement que le peuple éthiopien les annulera en s'y opposant à l'unisson. L'U.C.D.E. croit aussi que le peuple du continent africain se tiendra toujours aux cotés du peuple éthiopien, car le peuple africain considère l'histoire de l'Éthiopie indépendante comme l'histoire de son indépendance, et la "langue du peuple libre" l'amharique comme la langue de sa propre liberté. 1: la machination. Le gouvernement "E.P.R.D.F.-Parti de la Prospérité" illégitime a été installé au pouvoir, suite à l'interférence du gouvernement des États Unis d'Amérique dans les affaires intérieures de l'Éthiopie souveraine, en mai 1991. Sans avoir le souhait ou le consentement du peuple éthiopien, le régime s'est contenté de suivre les directives illicites qui lui ont été dictées, pour appliquer sa "nouvelle politique des langues" consistant à reléguer la langue amharique de sa position de langue officielle à celle de "langue de travail du gouvernement". Ce faisant, il a, durant les 29 dernières années, sapé de manière systématique la langue amharique, tout en laissant la porte grande ouverte à la langue anglaise et en dépensant l'argent du contribuable éthiopien pour la promotion de cette langue étrangère. De plus, le régime encourage ouvertement tous ses apparatchiks, en commençant par le "premier ministre", à utiliser leur présence médiatique pour populariser l'habitude déplorable de mélanger l'anglais dans leurs déclarations officielles en amharique, cela avec un mépris total pour le pays et le peuple qu'ils prétendent servir. De toutes les occasions, le régime a maintenant choisi les célébrations de la Victoire d'Adwa pour rendre publique ces politiques disruptives et destructives qui étaient en préparations sous les auspices de quelques intellectuels dont nous sommes obligés maintenant de qualifier de mercenaires intellectuels de l'impérialisme. 2: cause et finalité de la machination. L'Éthiopie est un pays souverain vieux de plusieurs millénaires, établie sur les bases de sa propre civilisation: "ሥልጡንሕዝብና". Des forces de l'impérialisme qui sont apparues puis disparues dans l'histoire, ont toutes essayé de subjuguer ou d'annihiler l'Éthiopie; mais comme la victoire éclatante d'Adwa nous l'a rappelé, elles étaient à chaque fois vaincues et repoussées. De même, les forces impérialistes d'aujourd'hui sont engagées dans une obstination malsaine visant à venir à bout de cette civilisation, en s'attaquant d'une part à son avenue: la langue amharique, et d'autre part en s'attaquant à son véhicule: l'écriture éthiopienne. L'amharique a été la langue de citoyenneté en Éthiopie durant trois millénaires, et, en remplacement de la langue g'z, elle est la langue de gouvernement depuis le 11ème siècle A.D.. Au cours de cette longue période, l'amharique, qui est par nature dotée de puissants attributs génératifs s'est transformée en une langue versatile et sophistiquée, surmontant un par un tous les obstacles qu'elle a rencontrés, pour servir le pays avec distinction et de manière fiable et satisfaisante; ce qu'elle continuera de faire à l'avenir. De même, la langue anglaise, en sa qualité de langue internationale de choix, a joué un rôle considérable dans les relations internationales de l'Éthiopie, et continuera à le faire à l'avenir. Les langues communales, nommément l'oromgna, le tgrigna, le somalgna et l'afergna, que le gouvernement "E.P.R.D.F.-Parti de la Prospérité" illégitime a choisi d'élever au rang de langue de travail du "gouvernement fédéral", au même titre que l'amharique (tout en ignorant d'autres langues communales comme l'aguewgna, le sidamgna, le guourag-gna, etc.). Ce faisant, le régime semble ignorer que ces langues ne sont pas les propriétés privées de quelques sections de la population, mais appartiennent bel et bien à l'unité du peuple éthiopien. Le peuple souverain de l'Éthiopie est l'unité des citoyens éthiopiens; qu'il soit béni de langues et traditions diverses témoigne de la nature civile et tolérante de son système politique pré-existant. Contrairement à ce que la "constitution apartheid" d'inspiration US proclame de manière erronée, le peuple éthiopien n'est pas un fatras de peuples mais un peuple de citoyens. Depuis la reconstitution de l'Éthiopie en un État de Droit, sous le règne de l'Empereur Mnilk Ier (974-949 avant J.C.), le peuple éthiopien est connu sous son nom constitutif de "Amhara" ou "Peuple Libre"; sa langue de citoyenneté a toujours été l'amharique. La citoyenneté éthiopienne requiert de par sa nature une seule langue de citoyenneté. Parce que l'amharique est la langue que le peuple citoyen a réalisé par son unité, elle a toujours gagné son respect, son amour et son adoption unanime. Il n'y a pas eu de moment dans l'histoire où le peuple éthiopien aurait demandé à ce que "la langue amharique soit déclassée de sa position de langue officielle à celle de langue de travail du gouvernement", ni un moment où il aurait demandé à ce que "chacune des 84 langues communales deviennent une langue de travail du gouvernement". Nous sommes forcés de déduire, dans les circonstances présentes, que la pression provient uniquement des forces de l'impérialisme dont les objectifs tactiques sont la disruption et la destruction. Avec l'impérialisme, il y a probablement aussi, un degré de manque de prise de conscience de la part des forces étrangères impliquées qui explique en partie leurs actions illicites. Ce que les éthiopiens appellent "ሀገር" en parlant de l'Éthiopie, par-delà et au-delà de l'identité ethnique, est en fait l'État de Droit que le peuple, réuni autour des idéaux de sa civilisation de Droit "ሥልጡንሕዝብና", a établi par son union avec le territoire sur lequel il habite. Le terme qui traduit le mieux "ሀገር" est le terme occidental de "Cité". L'Éthiopie a dépassé le statut d'État fondé sur l'ethnicité, il y a de cela 3000 ans. Respectueuse des droits citoyens, dans toute son histoire, l'Éthiopie a été un refuge pour les victimes de persécution. Au 5ème siècle A.D., sous le règne de l'Empereur Elaméda (478-486 A.D.), elle accorda refuge à neuf saints de l'Église Orthodoxe Tewahdo pourchassés de Rome, de l'Égypte et de la Syrie par l'mpérialisme romain, et leur permit la pratique de leur foi en toute liberté, avec leurs coreligionnaires, en Éthiopie. Aujourd'hui, l'Église Orthodoxe Tewahdo Éthiopienne compte quelques 79 millions de fidèles en Éthiopie. Au 7ème siècle A.D., sous le règne de l'Empereur Adrʼaz (602-623 A.D.), les adeptes de l'Islam s'enfuirent vers l'Éthiopie lorsque les gouverneurs de la Mecque les persécutèrent. Ils choisirent l'Éthiopie parce que leur Prophète Mouhammed leur avait dits que c'était un pays où personne n'était persécuté. Aujourd'hui, l'Éthiopie compte quelques 18 million de musulmans éthiopiens qui y pratiquent leur foi en toute liberté. Le concept de citoyenneté est enraciné dans l'esprit du peuple éthiopien, et imprègne sa culture politique. Une preuve récente de cela est la manière avec laquelle la province de Bahr Mdr (Érythrée) qui était séparée de sa mère patrie l'Éthiopie par le colonialisme, a finalement été réunie à l'Éthiopie. En 1952, le Bahr Mdr fut rattachée à l'Éthiopie suite à l'adoption par les Nations Unies d'une résolution entérinant le souhait de la majorité des habitants du territoire. Néanmoins, contrairement à l'union pure et simple que souhaitait la population du territoire, les Nations Unies décidèrent d'opter pour le format fédéral, lequel était anathème à l'esprit éthiopien. Dix années plus tard, en 1962, le "Bayto" ou parlement du Bahr Mdr passât à l'unanimité la résolution rejetant la fédération en faveur de l'unification avec l'Éthiopie. Le Bahr Mdr devint alors la 14ème province de l'Éthiopie suite à la ratification et au passage de la proclamation par le parlement éthiopien, la même année. Les éthiopiens perçoivent le peuple éthiopien en termes de citoyenneté, et non en terme de partition de différentes ethnies comme le stipule la "constitution d'apartheid" d'inspiration étrangère du régime R.F.D.E. Certains des pays qui sont encore établis sur les principes de l'état-nation, et qui de ce fait se considèrent à leurs yeux, à la pointe de l'évolution de l'État, ont pris des mesures déplacées et illégales consistant à imposer par la force la partition rétrograde de l'Éthiopie sur la base de l'ethnicité avant de la reconstituer derechef en une fédération ou confédération. Ces actes rétrogrades, autant qu'ils sont une interférence dans les affaires intérieures d'un pays souverain, sont nuls et non avenus; le peuple éthiopien ne les a pas acceptés et finira par les supprimer. En laissant de côté les statistiques à but de propagande qui sont largement diffusées, les données statistiques éthiopiennes concernant les locuteurs des différentes langues éthiopiennes, telles qu'elles sont observables sur le terrain, sont comme suit: •L'amharique est la langue de citoyenneté d'un pays de 110 million d'habitants; il est parlé partout dans le pays, et est enseigné dans chacune de ses écoles; •Avec l'amharique: ‣15% des locuteurs parlent l'oromgna (15.4%, si l'on inclus les locuteurs kényans); ‣8% des locuteurs parlent le tgrigna (y compris le Bahr Mdr); ‣5% des locuteurs parlent le somalgna (17%, si l'on inclus les locuteurs somaliens, kényans et djiboutiens); ‣1.7% des locuteurs parlent l'afergna (2%, si l'on inclus les locuteurs djiboutiens); Essayer d'imposer par "décret" que ces quatre langues communales et l'amharique deviennent les "cinq langues de travail du gouvernement fédéral", constitue une violation de la "Constitution" même du régime, dont l'article 5 stipule que: "l'amharique sera la langue de travail du gouvernement fédéral". Plus significativement, dans un pays où l'amharique a toujours été la langue de citoyenneté, un tel "décret" n'a aucune justification politique ou économique autre que le dessein malveillant d'entraver l'administration du pays, de contrecarrer sa croissance, de diviser le pays pour mettre en place un système confédéral dans la corne de l'Afrique et, éventuellement, d'imposer l'anglais comme unique langue de travail du gouvernement, pour finalement établir, selon la tactique de "diviser pour régner", un bastion de l'impérialisme dans la région; bref, pour livrer le pays aux mains de puissances étrangères. 3: opposition et lutte. Toute décision du gouvernement "E.P.R.D.F.-Parti de la Prospérité" illégitime portant atteintes aux intérêts permanents de l'Éthiopie est, a priori, nulle et non avenue. Néanmoins, si le régime persiste et applique ses dernières décisions pernicieuses sans aucun souci de légalité, comme nous l'avons témoigné jusqu'à présent, alors il est clair que suite à l'élimination du régime, ses officiels et collaborateurs seront tenus responsables et comparaîtront devant la justice. Partout dans le monde, nous vivons une époque de dangers imminents. Depuis le "nettoyage ethnique" jusqu'à l'éventualité d'une guerre civile totale, depuis la pauvreté jusqu'à la famine, depuis la corruption jusqu'aux abus des droits humains, depuis le trafic illégal des êtres humains jusqu'à la dispute autour du "barrage de la Renaissance", depuis le fléau de locustes jusqu'à la pandémie du "corona virus", les dangers auxquelles l'Éthiopie est confrontée sont graves. Le reste du monde aussi est harcelé par une liste sans fin de périls imminents. Dans ces conditions, nous devrions nous attendre à ce que toutes les parties responsables donnent la priorité aux solutions pacifiques, et respectent la légalité. Les dangers qui menacent notre pays ne peuvent être adressés qu'avec toutes les potentialités du pays entre les mains d'une autorité légitime. C'est pourquoi l'U.C.D.E., encore une fois, lance son appel au gouvernement "E.P.R.D.F.-Parti de la Prospérité" illégitime de reconnaître ces faits, de cesser de servir d'instrument aux puissances étrangères et de quitter le pouvoir pour laisser la place à un gouvernement de transition élu démocratiquement. Nous ne devons pas oublier une vérité essentielle cependant: tout corps organisé qui usurpe les instruments du pouvoir étatique est enclin et forcé à se soumettre aux puissances étrangères et servir leurs intérêts afin de se maintenir au pouvoir. Si l'Éthiopie a réussi à réaffirmer sa souveraineté et sauvegarder sa liberté avec la victoire d'Adwa, il y a 124 ans, sous l'habile direction de l'Empereur Mnilk II, c'est parce que celui-ci était le chef légitime d'un système politique éthiopien dont le mérite est d'avoir assuré durant trois millénaires l'indispensable principe de légitimité de l'autorité. Lorsque l'on examine l'histoire ancienne et contemporaine de l'Éthiopie, on s'aperçoit que les occasions où le pays a connu la défaite entre les mains des forces étrangères coïncident la plupart des temps avec les périodes de faiblesse où des usurpateurs sont à la tête du pays. Aujourd'hui, à moins que le peuple éthiopien ne réaffirme sa souveraineté, ne rétablit son État de Droit démocratique sur la base d'une nouvelle Constitution, et n'élit démocratiquement son gouvernement, les machinations de l'impérialisme, dont on ne voit ici que la pointe, finiront sans doute et dans un retournement lâche subit, par se transformer en un attentat contre l'existence même du pays. Le peuple éthiopien relèvera ce défi d'une manière organisée, en renforçant, à travers son engagement actif et patriotique, l'incarnation de son unité populaire qu'est l'U.C.D.E.. Secrétariat du Conseil Exécutif Provisoire, U.C.D.E.