Ethiopians' Citizen Democratic Union•Union Citoyenne Démocratique des Éthiopiens
aimbasic documentsslttunhzbnnalinks
Wazéma System•Wazéma Système
Awdeqelem text processor•traitement de text Awdeqelem DOWNLOAD
Ethiopians' Citizen Democratic Union•Union Citoyenne Démocratique des Éthiopiens

 ልዩ፡ማሳሰቢያ | Speci al Notice | Notice spéciale
"የቍ.1፡ መሠረታዊ፡ሰነድ፡ማሻሻያ። " (PDF)

ልዩ፡ማሳሰቢያ | special annoucement | annonce spéciale
"የኢ.ሀ.ሥ.አ.፡መሠረታዊ፡ሰነድ፡ጸድቋል።"
የኢ.ሀ.ሥ.አ.፡ጊዜያዊ፡ፈጻሚ፡ምክር፡ጽሕፈት፡ቤት። (PDF)

መሠረታዊ፡ሰነድ።
የኢ.ሀ.ሥ.አ.፡መሠረታዊ፡ሰነድ፡(PDF)።
 

ንግግር | Interview | Entretien
    የመሠረታዊ፡ሰነድ፡ዕደሳ፡ማብራሪያ
    የኢ.ሀ.ሥ.አ.፡ጊዜያዊ፡ፈጻሚ፡ምክር፡ጸሓፊ፥
    አቶ፡ወሌ፡ነጋ፥
    ከሥልጡንሕዝብና፡መዜንው፡ጋራ፡የተናገሩት። (PDF)

 

sl_SH_IHaSA

ዐውደ፡ቀለም፡የጽሑፍ፡ማምረቻ፡ዐዲሱ፡ክለሳ፡(ክ.1.3)።
The latest version (v.1.3) of AwdeQelem text processor.
La dernière version (v.1.3) du traitement de texte AwdeQelem.

     

    www.slttunhzb.net sh1@ttomar.net

    መሠረታዊ፡ሰነድ_20111230

    ነሐሴ፡30፡ቀን፥ 2011፡ዓ.ም.።

     

    መሠረታዊ፡ሰነድ።

    (ቍ.፡1፡መሠረታዊ፡ሰነድን፡ዐድሶና፡አጽንቶ፡የተካ።)

     

    እኛ፥ ከኢትዮጵያ፥ ከእየኅብረተሰቡ፡መወለዳችን፥ ከምድሯ፥ ከእየግዛቱ፣ ከእየከተማውና፡ከእየቀበሌው፡መምጣታችን፥ ሀገራችን፡ኢትዮጵያን፥ መላ፟ዋን፡ለመሠየምና፡አንድነቷን፡ለመመሰ፟ል፡የፈቀደልን፡ሀገራውያን፡ኢትዮጵያውያን፤

ነፍስ፡ወከፍ፡ባሕርያዊ፡መብታችንንና፡ሕዝባዊ፡የገዢነት፡ሥልጣናችንን፡ለሚጠብቅልን፡ርትዓዊ፡ኹነቷ፡(የርትዕ፡መንግሥቷ)፡በመቆም፥ በኢትዮጵያ፡ሥልጣን፡ሰገነት፡ላይ፡አላግባብ፡የወጣን፡ኀይል፡ዅሉ፡በመቃወም፥ ያልተጨቈነ፡ኅሊናዋን፡ምርጫ፡ለመናገር፥ ያልተገደደ፡ፈቃዷን፡ለመከተል፡ወደ፟ን፤

ሀገራዊ፡አንድነቷን፡የማጽናት፥ ሐራነቷን፡የመጠበቅ፥ እግዚእናዋን፡የማስከበርና፡ሥልጡንሕዝባዊ፡የርትዕ፡ኹነቷን፡(የርትዕ፡መንግሥቷን)፡የማቆም፡ሀገራዊ፡ተግባራችንን፡ለመፈጸም፡ቈርጠን፡መነሣታችን፥

      በስሟ፡ለመወ፟ከልና፡በሙሉ፡ሥልጣኗ፡ለመሥራት፡መብት፡የሚሰጠን፡ሀገራውያን፡ኢትዮጵያውያን፥ በቍ.፡1፡መሠረታዊ፡ሰነድ፡የተመለከተውን፡ዐድሰንና፡አጽንተን፥ የሚከተለውን፡ወስነን፥ በስሟ፡ዐውጀናል።

       

      ዐዋጅ።

      አንቀጽ፡1፤

      የኢትዮጵያ፡ኹነትና፡አገዛዛዊ፡ፍልስፍና።

1.1፤ በታሪኳ፡እንደተጻፈው፥ ኢትዮጵያ፥ በ1260፡ዓ.ም.፡ላይ፥ መላ፟ው፡ሕዝቧ፥ በሕገኛዎች፡ወኪሎቹ፡ሰውነት፥ በውዴታው፡ተሰብስቦ፥ በነጻነት፡መክሮና፡ዘክሮ፣ ወስኖ፥ በቃል፡ኪዳኑ፡አጽንቶ፥ በገቢር፡ባቈየው፡ደገ፟ኛ፡ዐፄ፡ሥሩ፡(ሥርዐተ፡መንግሥቱ)፡መሠረት፥ እያንዳንዱ፡ሀገራዊ፥ የብጤውን፡ባሕርያዊ፡መብት፡በማክበር፡ወንፈል፥ በኅብረቱ፡የሠራት፥ በፈቃዱ፡የከወናት፥ አንዲት፣ የማትከፋፈልና፡ሥልጡንሕዝባዊት፡ሐራ፡የርትዕ፡ኹነት፡ናት።

1.2፤ የኢትዮጵያ፡ሕዝብ፡እግዚእ፡(ገዥ)፡ነው። ኢትዮጵያን፡አዃኚው፡ሥልጣን፥ ዃኚው፡ፈቃድና፡ኹኑ፡አካል፥ ወይ፡ባንድ፡ቃል፥ ምኳኑ፥ የኢትዮጵያ፡ሕዝብ፡እና፡የሰፈረበት፡ብሔር፡[ምድር]፡አንድነት፡ነው። በሌላ፡አነጋገር፥ አንጋሹ፣ ነጋሹና፡መንግሥቱ፥ ወይም፡ገዢው፣ ተገዢውና፡ግዛቱ፡የኢትዮጵያ፡ሕዝብ፡እና፡የብሔሩ፡[የምድሩ]፡አንድነት፡ነው።

1.3፤ የኢትዮጵያ፡ብሔር፥ በሦስቱም፡አኳያዎቹ፥ በየብስም፡በባሕርም፡ባየርም፥ በርትዓዊ፡መዋሐድ፡ከመስፋት፡በቀር፥ የማይሸረፍ፣ የማይቀነስ፣ የማይጠብ፡ሙሉ፡ነው።

1.4፤ ኢትዮጵያ፡አንዲትና፡የማትከፋፈል፡ሀገር፡ናት።

       

      አንቀጽ፡2፤

      የሥልጣን፡ተገቢነትን፡ስለ፡ማረጋገጥ።

2.1፤ የኢትዮጵያ፡ሕዝብ፥ ከማንኛውም፡ጊዜ፡የበለጠ፡ባስተባበረውና፡ባስፋፋው፡የየካቲት፡ወር፡1966፡ዓ.ም.፡ሀገራዊ፡ንቅናቄው፡ኀይል፥ ቀዳማዊ፡ኀይለ፡ሥላሴ፡የያዙበትን፡የግዛት፡መብቱን፡በሰላም፡ሲያስመልስ፥ ላዲስ፡አበባ፡ከተማ፡ሰጥታ፡የተሰማሩትን፡ሰራዊቶች፡ለማስተባበር፡የተመደበው፡ወቷደራዊ፡ደርግ፤

2.1.1፤ ሊጠብቀው፡የቆመለትን፡ሕዝብ፡ከድቶ፥ የተውጣጣባቸውን፡ደንቦች፡አታሎ፥ ከርክክቡ፡መኻከል፡ሥልጣኑን፡በውንብድና፡አስጥሎ፥ የትግሉን፡መልካም፡ውጤት፡አጨናግፏል፥ የንቅናቄውንም፡ደገ፟ኛ፡ጕዞ፡አቋርጧል፤

2.1.2፤ ለፍትሕ፡ችሎትና፡ለሀገራዊ፡ሥልጣን፡የሚውለውን፡የመንግሥት፡ኀይል፥ በእጀ፡መናኛ፡ይዞ፥ የግፍ፡መኪናው፣ የግል፡መሣሪያው፡አድርጎ፥ በምቀኝነት፡በቀል፣ በእብሪት፡ሰውን፡በመፍጀት፥ የመላውን፡ሕዝብ፡ሰላምና፡ሰጥታ፡አደፍርሶ፥ ኢትዮጵያን፡እሥልጣን፡ጦርነት፡ውስጥ፡ዶሏል።

2.2፤ የሥልጣን፡ጦርነቱ፡ተቀጣጥሎ፥ በግንቦት፡ወር፡1983፡ዓ.ም.፥ በኢ.ሕ.ዴ.ሪ. ⁽⁾፡ይዘት፡መፍረስ፡ዋዜማ፥ የተባበሩት፡ያሜሪካ፡ኹነቶች፡(ዩውናይተድ፡ስቴይትስ፡ኦፍ፡አሜሪካ)፡መንግሥት፥ በኢ.ሕ.ዴ.ሪ፡ይዘት፡ተወካዮችና፡በተቀናቃኞቹ፡መኻከል፥ በብሪታንያ፡መዲና፡ለንደን፥ በሸምጋይነት፡የቀጠረው፡የዕርቅ፡ጉባኤ፤

2.2.1፤ ገና፡ከመዠ፟መሩ፥ በሸምጋዩ፡መንግሥት፡ክዳት፡ተጨንግፏል፤

2.2.2፤ ዕርቅ፡ሳይወርድም፥ ኢ.ሕ.አ.ዴ.ግ. ⁽⁾፡እና፡ሕ.ግ.ሐ.ኤ. ⁽⁾፡ዐዲስ፡አበባ፡ገብተው፡አገሪቱን፡እንዲቈጣጠሩና፥ የ"ሽግግር፡መንግሥት"ን፡እንዲመሠርቱ፤ ቀጥሎም፥ የክፍለ፡ሀገር፡ኤርትራን፡መገ፟ንጠል፡እዳር፡እንዲያደርሱ፡ሸምጋዩ፡መንግሥት፡አላግባብ፡በማዘዙ፥ የተባበሩት፡መንግሥታትን፡ሥምረት፡ረምርሟል፥ ባንዲት፡እግዝእት፡ሀገር፡የውስጥ፡ጕዳይ፡ጣልቃ፡ገብቷል፤ የጣልቃ፡ገብነት፡ውሳኔውንም፡አስፈጽሟል፤

2.2.3፤ በኢትዮጵያ፡ውስጥ፡ሕገ፡ወጥነትንና፡ውንብድናን፡አጽንቷል፤

2.2.4፤ ዕርቅ፡ባልወረደበት፡ቀውጢ፡ኹኔታም፥ የሕገ፡መንግሥት፡ማርቀቅ፡ኺደትን፡አስዠምሯል፥ የማርቀቁንም፡ኺደት፡በመቀየስ፥ የኢትዮጵያን፡ሕዝብ፡"ሕዝቦች"፡በማለት፡ህልውናውን፡የካደ፣ ፀረ፡ኢትዮጵያ፡የ"አፓርትሀይድ፡ሕገ፡መንግሥት"ን፡በሀገሪቱ፡ላይ፡በእጀ፡መናኛ፡ጭኗል፤

2.2.5፤ የኢትዮጵያን፡ሕዝብ፡ለዕልቂት፣ ለጭቈናና፡ለስደት፥ ሀገሪቱንም፡ለብዝበዛ፡ዳርጓል።

2.3፤ ከ2007፡ዓ.ም.፡እስከ፡2010፡ዓ.ም.፡ተጠናክሮ፡በቀጠለው፡ሀገራዊ፡እግዚእናን፡የማስመለስ፡ሕዝባዊ፡እንቅስቃሴ፡ምክንያት፥ የኢ.ፌ.ዴ.ሪ. ⁽⁾፡ይዘት፡ለ"ሥር፡ነቀል"፡ለውጥ፡ዝግጁ፡መኾኑን፡አስታውቋል፤ በተግባርም፡ምልክቶችን፡አሳይቷል።

2.4፤ የኢትዮጵያን፡ሕዝብ፡እግዚእና፡በማክበር፥ በሕጋዊ፡ሥልጣን፡ብቻ፡ሊሠ፟ራ፟በት፡የሚገባውን፡መንግሥታዊ፡ኀይል፥ የሕዝብ፡ይኹንታን፡ላገኘ፡ለባለዐደራ፡የሽግግር፡መንግሥት፡በማስረከብ፥ ዐዲስ፡ሕገ፡መንግሥት፡ተረቆ፟፡የሚጸድቅበትንና፡ዘላቂው፡ሥልጡንሕዝባዊ፡መንግሥት፡የሚቋቋምበትን፡ሕጋዊ፡አገባብ፡በጋራ፡ለማስለጥ፡ ኢ.ሀ.ሥ.አ.፡ይተጋል።

2.5፤ መላ፟ው፡የኢትዮጵያ፡ሕዝብ፥ በነጻና፡ሥልጡንሕዝባዊ፡ምርጫ፡ሠይሞ፡የሚያቋቁመው፡ሀገራዊ፡ከዋኝ፡ጉባኤ፦

2.5.1፤ በተወሰነለት፡ጊዜ፡ውስጥ፥ በሙሉ፡ነጻነት፡መክሮና፡ዘክሮ፡የሚያረቀ፟ውን፡ዐዲስ፡ሕገ፡መንግሥት፡ለሕዝብ፡አቅርቦ፡በማስጸደቅ፥

2.5.2፤ በሕገ፡መንግሥቱም፡መሠረት፡ዐዲሱን፡ሥልጡንሕዝባዊ፡የርትዕ፡ኹነት፡(የርትዕ፡መንግሥት)፡በማቆም፥

የሥልጣን፡ተገቢነትን፡በሀገሪቱ፡መልሶ፡ማስፈን፡የዚህ፡ሀገራዊ፡ሱታፌ፡አንድያ፡ዐላማ፡ይኾናል።

2.6፤ ይህም፡ዐላማ፡እዳር፡እስካልደረሰና፡የሥልጣን፡ተገቢነት፡በሀገሪቱ፡እስካልሰፈነ፡ድረስ፥ አንዳች፡ደገ፟ኛም፡ኾነ፡ክፉኛ፡ለውጥ፡በሀገሪቱ፡ቢከታተል፥ የሕዝብን፡እግዚእና፡ለዘለቄታው፡የማስከበሩ፡ሰላማዊው፡የኢ.ሀ.ሥ.አ.፡ትግል፡እስከ፡ሙሉ፡ክንዋኔው፡ድረስ፡ሳይቋረጥ፡ይቀጥላል።

 

      አንቀጽ፡3፤

      የኢትዮጵያ፡ሕዝብ፡ሕጋዊ፡ትግል።

3.1፤ የኢትዮጵያ፡ሕዝብ፥ ያገሩን፡ርትዓዊ፡ኹነት፣ የግዛቱን፡ሥልጡንሕዝባዊነትና፡ነፍስ፡ወከፍ፡ነጻነቱን፡የሚጠብቅበትን፡የገዢነት፡መብቱን፡ለማስከበር፥ በተናጠልም፡ኾነ፡በኅብረት፥ ወይ፡በሀገር፡ደረጃ፥ በየጊዜው፡የሚፈጽማቸው፡የፍትሕ፡ክርክሮች፥ ወይም፡የመሣሪያ፡ትግሎች፥ የጭቈና፡ተቃውሞ፡መብቱ፡የሚፈቅድለት፡ተገቢዎች፡ተግባሮች፡ናቸው።

3.2፤ የኢትዮጵያ፡ሕዝብ፥ ማንኛውንም፡ዐምባ፡ገነንነት፡ለመቃወም፡የሚያነሣው፡ጠቅላላ፡ትግል፥ ያልሞት፡ባይ፡ተጋዳይነት፡ብቻ፡ሳይኾን፥ ነፍስ፡ወከፋዊና፡ሀገራዊ፡እግዚእናውን፡የመከላከልም፡የተቀደሰ፡መብቱ፡ነው።

3.3፤ ለግል፡ጥቅም፥ ወይም፡ለውጭ፡ኀይል፡መሣሪያ፡በመኾን፡ኢትዮጵያን፡ለመቍረስ፣ ለመክፈል፣ ለማጥፋት፣ በከፊል፡ወይ፡በመላዋ፡ለባዕድ፡አሳልፎ፡ለመስጠት፥ በነፍስ፡ወከፍም፡ኾነ፡ባንዳች፡ኅብረት፡የሚሠራ፡ኹሉ፡የኢትዮጵያ፡ጠላት፡ነው።

 

      አንቀጽ፡4፤

      ቍርጥ፡ሐሳብ።

4.1፤ ኢትዮጵያን፥ ከወደቀባት፡ጥፋት፡አኹን፡የሚያድናትና፡ርትዓዊ፡ኹነቷን፡መልሶ፡የሚሠራላት፡ችሎት፥ የሕዝቧ፡አንድነት፡የሚያለማላት፡ሀገራዊ፡እግዚእናዋ፡መኾኑን፡ተገንዝበን፤

4.1.1፤ ተወላጇ፡የሚመኘውን፡የባለቤትነትና፡የነጻ፡ኅብረ፡ሰብእ፡ኑሮን፡የሚያገኘው፥ ሕዝቧ፥ ራሱን፣ በራሱ፣ ለራሱ፡ሲገዛ፡ብቻ፡መኾኑን፡ተረድተን፤

4.1.2፤ እነዚህንም፡መሠረታውያን፡ጸጋዎች፡የሚያጐናጽፋት፡ችሎት፥ የተወላጇ፡ባሕርያዊ፡ሥልጡንሕዝብና፡መኾኑን፡አምነን፤

4.1.2.1፤ የሕዝቧን፡አንድነት፡በመሥራት፥ ሀገራዊ፡እግዚእናዋን፡ለማልማት፤

4.1.2.2፤ ሰራዊቶቿን፡እትእዛዟ፡ሥር፡በመመለስ፥ የለውጡን፡ሰላማዊ፡ንቅናቄ፡ለማስለጥ፤

4.1.2.3፤ የኢትዮጵያ፡ሕዝብ፥ በጠቅላላ፡ንቅናቄው፡በባሕርያዊ፡ባለመብትነት፡የሚጠይቀውን፡የግዛት፡ሥልጣን፡ለማስከበርና፥ ሥልጡንሕዝብናን፡በኢትዮጵያ፡መልሶ፡ለማስፈን፥ ቅዱስ፡ለገቻ፡ገብተናል፤ ለገቻችንንም፡እፍጻሜ፡ሳናደርስ፡ላናርፍ፥ ላንመለስ፡ቈርጠናል።

4.2፤ ቍርጥ፡ሐሳባችንን፡እመልካም፡ፍጻሜ፡ለማድረስ፦

"የኢትዮጵያውያን፡ሀገራዊ፡ሥልጡንሕዝባዊ፡አንድነት – —ኢ.ሀ.ሥ.አ."

በተሠኘ፡መጠሪያ፥ አንድነታዊ፡አካላችንን፡አቁመን፥ ግብሩን፡ያከናውንልን፡ዘንድ፥ ባምስተኛው፡አንቀጽ፡የተመለከተውን፡ፈጻሚ፡ምክር፡ሠርተን፥ ሕዝባዊ፡ሥልጣናችንን፡ሠይመነዋል።

 

      አንቀጽ፡5፤

      የኢ.ሀ.ሥ.አ.፡ፈጻሚ፡ምክር።

5.1፤ የኢትዮጵያውያን፡ሀገራዊ፡ሥልጡንሕዝባዊ፡አንድነት፥ በአንቀጽ፡4፡የተመለከተውን፡ቍርጥ፡ሐሳባችንን፡በገቢር፡ያከናውንልን፡ዘንድ፥ አንድ፡ሀገራዊ፡ፈጻሚ፡ምክር፡ይኖረዋል።

5.2፤ ፈጻሚ፡ምክሩ፦

አንድ፡ሊቀ፡መንበር፤

አንድ፡ምክትል፡ሊቀ፡መንበር፤

ሦስት፡አባሎች፤

አንድ፡በዥሮንድ፤

አንድ፡ጠቅላይ፡ጸሓፊ፤

በድምሩ፡ሰባት፡በስም፡የመረጥንለት፡መማክርት፡ይኖሩታል።

5.3፤ በየኀላፊነቱ፡የሚያስቀምጣቸውን፡ባለሥልጣኖች፡ፈጻሚ፡ምክሩ፡ይሠይማል።

5.4፤ ፈጻሚ፡ምክሩ፡ሥራውን፡የሚያከናውንበት፡አንድ፡ሀገራዊ፡መሥሪያ፡ቤት፡ይኖረዋል። መንበሩን፡እተመቸው፡ቦታ፡የማድረጉ፡ምርጫ፡የርሱ፡ነው።

5.5፤ ፈጻሚ፡ምክሩ፡የውስጥ፡ደንቡን፣ የዘርፍ፡ጉባኤዎቹን፣ የክፍል፡መሥሪያ፡ቤቶቹን፡ደረጃና፡ብዛት፣ የሠራተኞቹን፡ዐይነትና፡መጠን፣ የሥራ፡ማስኬጃውን፡ራሱ፡ይወስናል።

       

      አንቀጽ፡6፤

      የኢ.ሀ.ሥ.አ.፡ፈጻሚ፡ምክር፡ግብር።

6.1፤ የውንብድና፡ይዘትን፡ከኢትዮጵያ፡አስወግዶ፡የኢትዮጵያን፡ሕዝብ፡እግዚእና፡መልሶ፡ማስከበር፤

6.2፤ እግዚእናውን፡ተረክቦ፡ከለበሰበት፥ ማለት፥ የውንብድና፡ይዘት፡ከተወገደበት፡ዕለት፡አንሥቶ፥ ከስድስት፡ወር፡በማያልፍ፡ጊዜ፡ውስጥ፥ የኢትዮጵያ፡ሕዝብ፡ሀገራዊ፡ኹነቱን፡በውዴታው፡እንዲከውን፥ ባልተጨቈነ፡ኅሊናው፥ ባልተጨነቀ፡ልቦናውና፡ባልተገደደ፡ፈቃዱ፡ዐዲስ፡ክዋኔን፡ወይም፡ሕገ፡መንግሥትን፡የሚሠራለትን፡ሀገራዊ፡ከዋኝ፡ጉባኤውን፡በሙሉ፡ነጻ ነትና፡በብሔራዊ፡መረጣ ⁽⁾፡ለማቋቋም፡የሚያሻውን፡ሰጥታና፡ምቾት፡ማረጋገጥ፤ የሚፈለገውንም፡ሙሉ፡አገልግሎት፡ማበርከት፤

6.3፤ ሀገራዊው፡ከዋኝ፡ጉባኤ፡ዐዲሱን፡ክዋኔ፡ከወሰነበት፡ዕለት፡አንሥቶ፥ መንፈቅ፡በማያልፍ፡ጊዜ፡ውስጥ፥ በዚሁ፡ክዋኔ፡መሠረት፥ ግዛቱን፡በሙሉ፡ነጻነት፡የሚያቋቁምበትን፡ምቾት፡ማረጋገጥ፤

6.4፤ ዐዲሱ፡ግዛት፡እስከሚቋቋምበት፡ቀን፡ድረስ፥ ታሪካዊውን፡የሀገሪቱን፡ሥርዐተ፡መንግሥት፡(ወይም፡ዐፄ፡ሥር)፡ፍልስፍናን፡ጠንቅቆ፡በማወቅና፡በማክበር፣ አሠራሩንም፡በማዘመን፥ አስቀድሞ፡በዝርዝር፡በተደነገገለት፡መመሪያ፡መሠረት፥ የሀገሪቱን፡ጠቅላላ፡አስተዳደር፡ማከናወን፤

6.5፤ ያዲሱ፡ግዛት፡ባለሥልጣኖች፡የሥራ፡መንበራቸውን፡በወግ፡በተረከቡበት፡ዕለት፥ ፈጻሚ፡ምክሩ፡ሥራውን፡ፈቶ፟፣ ስፍራውን፡ለቆ፟፡መበተን፡ይኾናል።

       

      አንቀጽ፡7፤

      የኢ.ሀ.ሥ.አ.፡ፈጻሚ፡ምክር፡ኀላፊነት፣ መብት፣ ሥልጣንና፡ዕድሜ።

7.1፤ የኢትዮጵያውያን፡ሀገራዊ፡ሥልጡንሕዝባዊ፡አንድነት፡ፈጻሚ፡ምክር፥ በኢትዮጵያ፡መንግሥት፡መብት፥ ኀላፊነትና፡ሥልጣን፡ይሠራል።

7.2፤ የኢ.ሀ.ሥ.አ.፡ፈጻሚ፡ምክር፡የሥልጣን፡ዕድሜ፥ በዚህ፡ጠቅላላ፡ውሳኔ፡የተነገረውን፡መልእክቱን፡በገቢር፡ከዠመረበት፡ጊዜ፡አንሥቶ፥ በንኡስ፡አንቀጽ፡6.5፡የተወሰነው፡እሚፈጸምበት፡ዕለት፡የሚደርስ፥ ከዚያ፡በፊት፡የማይመለስ፥ ከዚያም፡በዃላ፡የማይታደስ፡ነው፨

 

       ሙሉ፡ስም ___________________

      ዘንዳ    __________________

      ሞያ    ___________________

       

       

© የኢትዮጵያውያን፡ሀገራዊ፡ሥልጡንሕዝባዊ፡አንድነት፡(ኢ.ሀ.ሥ.አ.)፥2008-2015፡ዓ.ም.።